ላለው የውጊያ አማራጭ ተጠያቂው እራሱ ህወሓት ነው – አቶ አባዱላ ገመዳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


«የሁለቱ ወገኖች ልዩነት የመጥበብ አዝማሚያን አላሳየም»

ሰሞኑን የፌዴራል መንግስት “ህወሃት ላይ ያነጣጠረ ነው” በሚል በትግራይ ክልል እየወሰደ ላለው የውጊያ አማራጭ ተጠያቂው እራሱ ህወሓት ነው አሉ የቀድሞው የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ አባዱላ ገመዳ፡፡

DW : የፌዴራል መንግስት ህወሃት ላይ እየወሰደ ላለው የውጊያ አማራጭ ተጠያቂው እራሱ ህወሓት መሆኑን አቶ አባዱላ ገመዳ ተናገሩ፡፡ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በተለያዩ የሃገሪቱ ከፍተኛ የስልጣን እርከኖች ላይ ሲሰሩ የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ በፌዴራሉ እና ትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው “ህወሓት” መካከል የነበሩ የሃሳብ ልዩነቶች ጦር ለመማዘዝም የማያበቁ እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡
ይሁንና ከብልጽግና ፓርቲ ምስረታ በኋላ “የሁለቱ ወገኖች ልዩነት የመጥበብ አዝማሚያን አላሳየም” ያሉት አባዱላ በተለይም ህወሓት “በፌዴራሉ መንግስትና በህገ መንግስቱም ጭምር እውቅና የተነፈገ” ካሉት የትግራዩ ምርጫ በኋላ ግን ነገሮች ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ማምራታቸውን እና የድርድር መስመርን ያጠበቡ ብለውታል፡፡
በህወሓት ባለስልጣንም ጭምር ተረጋግጧል ያሉት የሰሜን ዕዝ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተወሰደው ያልታሰበ ያሉት ጥቃት ደግሞ “የፌዴራሉ መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት ለመግባቱ ማሳያ ነው” ያሉት አቶ አባዱላ አሁን ሊደርስ የሚችለውን ቀውስ የሚያሳንሰው የጦርነቱን ጊዜ ማሳጠር ብቻ ነው ሲሉም አክለዋል።