ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ተወያዩ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ተወያዩ።
በውይይቱ ወቅት የሕወሓት ጁንታ ከዚህ የባሰ ጥፋት ከማድረሱ በፊት በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርብ፣ የከተማው ሕዝብ እንዳይጎዳ ሕግ ለማስከበር በሚደረገው ዘመቻ በከተሞች አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ስምምነት መደረሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በጁንታው ግጭት ቀስቃሽነት ምክንያት የተፈናቀሉ ትግራዋይን ለመመለስና ለመርዳት በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በኩል የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውይይት ተደርጎ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ሕግ የማስከበር ዘመቻው ሲጠናቀቅ ትግራይን መልሶ ለማቋቋም የተዘጋጀው ዕቅድ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።