የአለም አቀፍ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን ከመቀሌ በማስወጣት ላይ ናቸው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአለም አቀፍ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን ከመቀሌና ከትግራይ አካባቢዎች በማስወጣት ላይ ናቸው

የተለያዩ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን ከመቀሌና ከትግራይ አካባቢዎች በማስወጣት ላይ መሆናቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለካፒታል ጋዜጣ ገልጸዋል።

አምባሳደሩ የተባበሩት መንግስታት ደርጅትን ጨምሮ ሐገራት ዜጎቻቸውንና ሠራተኞቻቸውን ከትግራይ ክልል እያስወጡ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን በትላንትናው እለት ብቻ ከ 200 የሚበልጡ የUN ሰራተኞች በአፋር ክልል በኩል የወጡ መሆኑን መናገራቸውን ካፒታል ዘግቧል።

ደርጅቶች ባላቸው የሳተላይት መገናኛ ከሠራተኞቻቸው ጋር በመገናኘት ከመቀሌ እስከ አፋር ክልል ድንበር ድረስ የክልሉ መንግስት ጥበቃ እያደረገላቸው የሚመጡ ሲሆን ከአፋር ክልል በዋላ የፌደራል መንግስትና ድርጅቶቻቸው የሚቀበሏቸው እደሆነ ገልጸዋልም ብሏል።

ይህ ሲሆን ሁሉም ድርጅቶች የሚያስወጧቸውን ሠዎች ዝርዝር ለፌደራል መንግስት መስጠትና ለወንጀል የማይፈለጉ መሆናቸው መረጋገጥ እንደሚኖርበት ተገልጿል።

በትግራይ ክልል የሚፈጠረውን የኑሮ ጫና ለማገዝ መንግስት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ለመስጠት ምቹ ሁኔታዎችን እየፈለገ ቢሆንም ከተፈጠረው ችግር ባሻገር ህውሓት መንገድና ድልድዮች ላይ ጥፋት መፈጸሙ ሁኔታውን ይበልጥ አስቸጋሪ አድርጎታል ማለታቸውን ሲል ዘገባው አካቷል።