የፅንፈኛው የሕወሓት ቡድን ሀገርን የመበተን ዓላማ ከሽፏል – ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሀኑ ጁላ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ህወሓት ከፍተኛ ሀይል ገንብቶ በጦርነት ወደ ስልጣን ለመመለስ አልያም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የነበረው እቅድ ከሽፎበታል -ጄኔራል ብርሀኑ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሀኑ ጁላ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ እየሰጡ ነው።
ህወሓት ሰራዊት በመገንባት እና ሚሊሻን በመጨመር ኢትዮጵያን ወደ ጦርነት በማስገባት ከቻለ ማሸነፍ ካልቻለ ኢትዮጵያን መበታትን እቅድ እንደነበረው በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

ሆኖም በተወሰደው እርምጃ የዚህ ሀይል እቅድ ሊከሽፍ ችሏል ነው ያሉት፡፡አሁን ላይ ሀይሉ የነፍስ አውጪኝ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛልም ብለዋል።

የጦር ሀይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ፣ ሠራዊታችን በሁሉም ግንባሮች ድልን እየተጎናፀፈ እንደሚገኝ አረጋገጡ ። ጁንታው እያንዳንዳቸው 2 ሺ 500 የሰው ሀይል የያዙ 11 ብርጌድ ልዩ ሀይል ፣ 14 ብርጌድ የዞን ታጣቂ እና አንድ ብርጌድ ሚሊሻ ቢገነባም ፣ አሁን ነፍስ አውጭኝ ላይ ይገኛል ብለዋል ።
ጀግናው ሠራዊታችን በምዕራብ ትግራይ ከዳንሻ – ባዕከር ፣ አዲጎሹ ፣ አዲ ሀገራይ ፣ አዲጉዞምን ሰብሮ ትናንት ሽሬን መቆጣጠሩን አረጋግጠዋል ።
በደቡቡ ግንባርም ከዋጃ ጀምሮ አላማጣ ፣ ኮረምን ይዞ ወደፊት ቀጥሏል ። በምስራቁ ግንባር ፣ ጨርጨር ፣ መሆኔ ፣ ራያ ቆቦና ሌሎች ቦታዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል ። ጁንታውን ለህግ ለማቅረብም ግስጋሴውን ቀጥሏል ።
ነጻ በወጣው አካባቢ የሚገኘው ህብረተሰብ ለሠራዊታችን ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጀነራል ብርሀኑ አስታውሰው ፣ ህዝቡ ሠራዊታችንን ከሁዋላው እንዲመታ ቢያስታጥቁትም ፣ ምንም ሳይተኩሱ 200 መትረየስና ክላሽ አዲኮኮብ እና ሽሬ ላይ ለሠራዊታችን እስረክቧል ብለዋል ።
ጁንታው ኮማንድ ፖስቱን እና ትኳሾቹን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቢያደርግም ሠራዊታችን ነጥሎ ለመምታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል ። በአሁኑ ሰዓት ጁንታው ኢትዮጵያን ወደ ጦርነት ለማስገባትና ለመበታተን ያቀደው እንደከሸፈበትና በመከበቡ ነፍስ አውጭኝ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል ።