ህወሓት በኤርትራ ላይ የፈጸመውን ጥቃት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር አወገዙ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በኤርትራ ላይ የፈጸመውን ጥቃት እና ግጭቱን ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ ያደረገውን ሙከራ አጥብቀን እናወግዛለን ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ፅፈዋል።

ህወሓት እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ግጭቱን ለማብረድ፣ ሰላምን ለማስፈን እና የሰላማዊ ሰዎችን ደሕንነት ለመጠበቅ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ማቅረባቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

The United States strongly condemns the attack carried out by the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) on the airport in Asmara, Eritrea, on November 14. We are deeply concerned by this blatant attempt by the TPLF to cause regional instability by expanding its conflict with Ethiopian authorities to neighboring countries. We also continue to denounce the TPLF’s November 13 missile attacks on the Bahir Dar and Gondar airports in Ethiopia.

ኤርትራ የአጸፋ እርምጃ ባለመውሰድ መታቀቧ ግጭቱ እንዳይስፋፋ ማገዙን ጠቅሰው አመስግነዋል።በተጨማሪ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኞች ለተጋላጮች ዕገዛ እንዲያቀርቡ ደሕንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ ሊፈቀድላቸው ይገባል ብለዋል ፖምፕዎ። የአሜሪካ ዜጎችን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎች ከጉዳት ሊጠበቁ ፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ ሊሰጣቸው እና ከግጭት ቀጠናው የሚወጡበት መተላለፊያ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ገለልተኛ የሆነ ዘገባ ለመስራት እንዲቻልና የአሜሪካ ዜጎችን ጨምሮ ከሰላማዊ ሰዎች መገናኘት እንዲቻል በትግራይ የተቋረጡ የመገናኛ አገልግሎቶች ወደ ሥራ ሊመለሱ እንደሚገባም መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

We strongly urge the TPLF and the Ethiopian authorities to take immediate steps to de-escalate the conflict, restore peace, and protect civilians. We appreciate Eritrea’s restraint, which has helped prevent further spreading of the conflict. Humanitarian workers should be given safe passage to provide assistance to vulnerable groups. Civilians, including U.S. citizens, should be protected from harm and be provided with humanitarian assistance and safe passage out of the conflict zones. Communications services in the Tigray region should be restored immediately in part to allow independent reporting on the situation and to allow for communication with civilians, including U.S. nationals, in the Tigray region.