በአርበኛ ምሬ ወዳጆ የሚመራው ምኒልክ ዕዝ እና በአርበኛ መከታው ማሞ የሚመራው ሸዋጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጋራ በካሄዱት ውጊያ ታላቅ ድል መጎናፀፋቸው ተሰምቷል።

በአርበኛ ምሬ ወዳጆ የሚመራው ምኒልክ ዕዝ እና በአርበኛ መከታው ማሞ የሚመራው ሸዋጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጋራ በካሄዱት ውጊያ ታላቅ ድል መጎናፀፋቸው ተሰምቷል።

በአይነቱ ለየት ያለ ወንድማማችነትና አንድነት የታየበት ጥምረት ተፈጥሮ፡ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ጠንካራ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ታውቋል።

ሁለቱ ኃያል ዕዞች ዛሬ ህዳር 23/2018 ዓ/ም ከረፋድ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ በደቡብ ወሎ ዞን ስር በደገርና አከባቢው ላይ ከባድ ትንቅንቅ ሲያካሂዱ ውለው አምሽተዋል።

በተመሳሳይ መረጃ ስትራቴጂክ የጦር ስፍራ እንደሆነ በሚነገርለት በደላንታ ወረዳ ስር በሚገኘው ፀሐይ መውጫ አከባቢ ላይ በተደረገ ተጋድሎ ፋኖ ድል መቀዳጀቱ ታወቀ!

በተመሣሣይ በዳውንት ወረዳ በተካሄደ አውደ ውጊያ ፋኖ አዳዲስ የጦር ስልቶችን በመጠቀም ኃያልነቱን ያስመሰከረበትን ተጋድሎ ማካሄዱ ታውቋል።

በዚህ ታላቅ ተጋድሎ ከባድ ጥቃት የተሰነዘረበት አገዛዙ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባ ሲሆን፡ የደላንታና የወገል ጤና የብልፅግና ካድሬዎች ተከበናል በሚል በዚህ ምሽት ወደ ደሴ ከተማ መሸሻቸውት ተሰምቷል። እንዲሁም በሌላ መረጃ ትናንት በሉማሜ ወረዳ ከተፈፀመበት ጥቃት ለጥቂት ተርፎ ሸሽቶ የነበረው የኦህዴድ ተላላኪው አቶ አረጋ ከበደና ቡድኑ፡ በደብረ ማርቆስ ከተማ ባካሄዱት ስብሰባ ከማሕበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ነቀፋና ውርደትን መከናነባቸው ተሰምቷል!

የልዩ ኃይሉ መፍረስ፣ በአገዛዙ የሚፈጸመው እገታ፣ ዘረፋ፣ ጅምላ ጭፍጨፋ፣ የንጹሐን ሞት፣ የገዳማት ውድመት፣ የመነኮሳት የቆሎ ተማሪዎች የካሕናት ጭፍጨፋ፣ ጡት ቆረጣ መሰል በአገዛዙ የሚፈፀሙ ግፎችን የጠቀሰው ማሕበረሰቡ፡ የዚህ ሁሉ አስፈፃሚዎች እናንተ ናችሁ በሚል ጣቱን ቀስሮባቸው እንደዋለ ታውቋል።

ነገሩ በጠበቁ ልክ ያልሆነላቸው እነአረጋ ከበደና ስብስቡ፡ በሕዝቡ አቋም በመደናገጥ የፅንፈኛ ተልዕኮን ተሸክሞ የሚንቀሳቀስን ሰው ለምን በስብሰባ አሳተፋችሁ በሚል በምስራቅ ጎጃም ዞንና በደብረማርቆስ ከተማ ካድሬዎች ላይ ከባድ ትችት መሰንዘራቸው ታውቋል።