" /> የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ሃላፊ ተክላይ ፀሃዬ ደብዛው አልተገኘም ክትትሉ ቀጥሏል። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ሃላፊ ተክላይ ፀሃዬ ደብዛው አልተገኘም ክትትሉ ቀጥሏል።

የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ሃላፊ ነበር። ተክላይ ፀሃዬ ይባላል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በክልሎች እየተንቀሳቀሱ ከህዝብ ጋር በሚወያዩባቸው ቦታዎች ሁሉ አብሮ ይዞር ነበር። የአካባቢዎቹን ፀጥታ በማስከበር ስራ ውስጥ አባል በመሆን ነው።

 

ሆኖም ግን ይህ ግለሰብ አልሳካለት አለ እንጂ በጉዞዎቹ ሁሉ የጥፋት ተልዕኮ ተሰጥቶት ሲያደባ እና ሲከሽፍበት ነበር። በስተመጨረሻም ከሰኔ 16ቱ የመስቀል አደባባይ የቦምብ ፍንዳታ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ተሰውረ። ደብዛው አልተገኘም። ክትትሉ ቀጥሏል።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV