በሕወሓት ጥሪ ራሳቸውን ከስልጣን ባሰናበቱት የሕወሓት አባሏ ሮማን ግብረስላሴ ምትክ ዶክተር አረጋዊ በርሔ ተሾሙ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Image may contain: 1 person, standing and outdoorዶክተር አረጋዊ በርሔ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ።
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ ለህወሐት መስራችና የቀድሞ አመራር ለነበሩት አቶ አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) ይህንን ሹመት መስጠታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
ከዚህ ቀደም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤትን በዋና ዳይሬክተር ሲያገለግሉ የነበሩት ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ ነበሩ።
ዶክተር አረጋዊ በርሄ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀ-መንበር መሆናቸው ይታወቃል።