አቶ ልደቱ አያሌው በድንገት አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰዳቸው ተሰማ፡፡


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
አቶ ልደቱ አያሌው በድንገት ከቢሾፍቱ ፖሊስ ጣቢያ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰዳቸው ተሰማ፡፡
ፖሊስ አቶ ልደቱንለምን ፖሊስ ወደ ፍርድ ቤት እንደወሰዳቸው እስካሁን ምንም መረጃ እንዳሌለው ፖርቲያቸው አስታውቋል፡፡
የዋስትና መብታቸውን ፖሊስ እንዲያከብር ለመነጋገር ፍርድ ቤት ቀጠሮ ሰጥቶን እየጠበቅን ባለንበት ሁኔታ ነው ዛሬ ከፖሊስ ጣቢያ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰዳቸውን የሰማነው ብለዋል የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዝደንት አቶ አዳነ ታደስ ለኤትዮ ኤፍ ኤም፡፡
አቶ አዳነ እንዳሉት አቶ ልደቱ ምንም አይነት መጥሪያ እንዳልደረሳቸው ብናውቅም በአንድ ሚዲያ ግን አቶ ልደቱ በሌላ ጉዳይ ክስ እንደተመሰረተባቸው የሚያሳይ ዘገባ ወጥቶ መመልከታቸው በእጅጉ በፍትህ ስርአቱ ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎናል ነው ያሉት፡፡
አቶ ልደቱ ፖሊስ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወሰዳቸው በኃላ ስለተፈጠረው ነገር ለማጣራት ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ እየተጓዙ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡