የፖለቲካ ፓርቲዎች ባልደራስ ያቀረበውን የአዲስ አበባን የራስ ገዝነት ጥያቄ እንደሚደግፉ ገለፁ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


  • የፖለቲካ ፓርቲዎች ባልደራስ ያቀረበውን የአዲስ አበባን የራስ ገዝነት ጥያቄ እንደሚደግፉ ገለፁ።
  • በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት ዛሬ በተካሄደው የፓርቲዎች የጋራ ምክክር ላይ ነው ይህንን ያሉት።
ምን ምን ነጥቦች ተነሱ…..
ተሳታፊ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን ሲገልፁ የአዲስ አበባ ጉዳይ እጅግ ይመለከተናል አብሮ መስራት በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ከአዲስ አበባ ራስ ገዝ አስተዳደር ጥያቄው በተጨማሪ …በተረኛው መንግስት አስተዳደራዊ በደል ላይ በጋራ ልንሰራ ይገባል። በተጨማሪም አገራዊ መግባባት እንዲመጣና ሕገ_ መንግስቱ እንዲለወጥ አብረን መስራት አለብን የሚሉ ሀሳቦች ተንሸራሽረዋል።
.ባልደራስ ጠንካራ አገራዊ አጀንዳዎችን እያመጣ ከፊት ሆኖ ለሚያደርገው ትግል እውቅና እንሰጣለን። የባልደራስ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ ከጅምሩ ያደርግ የነበረውን ትግል አደንቃለሁ። ብለው የተናገሩ የፖለቲካ አመራርም ነበሩ።
የአዲስ አበባ መዋቅራዊ ችግር ይፈታል ብለን የምናምነው ሕገ_መንገስቱ ሲቀየር ነው ብለው እንደሚያምኑ ፓርቲዎቹ ደጋግመው ገልፀዋል። በስተመጨረሻ ፓርቲዎቹ ውይይቱ ሁሉን አካታች ውይይት መሆን እንደሚኖርበት የተወያየዩ ሲሆን ለመነሻ ዛሬ የተወያዮት ፓርቲዎች ባልደራስን ጨምሮ 6 ፓርቲዎች ነበሩ።
በዛሬው ቀን የተሰበሰቡት ፓርቲዎች ሰብሰባውን ሲደመድሙ በሶስት ሳምንት ውስጥ እንደገና ተገናኝቶ ለመወያየት ወስነዋል።