የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ80 ሚሊየን ዶላር እርዳታ አጸደቀ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ግብርና እና ለአርሶ አደሮች ድጋፍ የሚውል የ80 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ማጽደቁን አስታወቀ።ባንኩ በድረ ገጹ ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳስታወቀው፣ እርዳታው የኢትዮጵያን ግብርና ምርት ለማሰደግ እና በእፕነስተኛ ማሳ ለሚተዳደሩ ለአርሶ አደሮች የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚውል ነው።
World Bank Provides Additional Support for Agriculture Growth and Better Livelihood Opportunities for Ethiopia’s Smallholder Farmers

የዓለም ባንክ የ 2019 የድህነት ምዘና በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ባለፉት አስርት ዓመታት ለድህነት ቅነሳው ቁልፍ አንቀሳቃሽ ዘርፍ መሆኑን ጠቅሶ ለሁለተኛው የግብርና ልማት ፕሮጀክት (AGPII) ተግባራዊነት የሚያግዝ ተጨማሪ ፋይናንስ ማጽደቅ ለአገሪቱን የግብርናው ኢኮኖሚ ማሳደግ አቅም ይፈጥራል ብሏል።

በአለም ባንክ ከፍተኛ የግብርና ባለሙያ የሆኑት ቪካስ ቹድሃሪ እንዳሉት “ሁለተኛው የግብርና ልማት ፕሮጀክት (AGPII) በኢትዮጵያ ድህነት ቅነሳ ላይ የጎላ አስተዋፅዖ አድርጓል ፡፡ ፕሮጀክቱ በተጨባጭ በተለይም ምርታማነትን በማሳደግ እና የንግድ ሥራን በማጎልበት ረገድ ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል ፡፡ በተጨማሪም የመስኖ አጠቃቀምን በማስተዋወቅ አርሶ አደሩ በአንድ ዓመት ውስጥ ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ ሰብሎችን ለመሰብሰብ አስችሎታል ፡፡ አርሶ አደሩ ዝናብ ላይ ጥገኝነት በመላቀቅ እሴት የሚጨምሩ የአትክልት ፍራፍሬዎችን ማምረት ጀምሯል።
በተለይም AGPII ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ አነስተኛ አርሶ አደሮች (37% ሴቶች የሆኑ ) የግብርና አገልግሎቶችን ተደራሽነት ለማሳደግ ረድቷል ፡፡ እንዲሁም በ 254 አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎች መጠቀም በመቻሉ በሰብል ምርታማነትን በማሳደግና በአየር ንብረት-ዘመናዊ ጥበቃ ላይ ውጤታማ መሆን ተችሏል ነው ያለው ባንኩ።
ፕሮጀክቱ አርሶ አደሮችን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር እንዲላመዱ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን 2 ሺህ 299 አዳዲስ አነስተኛ የመስኖ እቅዶችን በማጠናቀቅ እና ነባር የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በማሳደግ 23,290 ሄክታር የእርሻ መሬት በመስኖ እንዲለማ አስችሏል ተብሏል ፡፡
በፕሮጀክቱ ስር የተካሄዱት የገበያ መሰረተ ልማት እና የእሴት ሰንሰለት ኢንቬስትመንቶች አርሶ አደሮችን ከገበያዎች ጋር በማስተሳሰር እና ንግድን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል ፡፡ እነዚህ ተግባራት በሄክታር ከፍተኛ የምርት መጠን እንዲጨምር በማገዛቸው የአርሶ አደሮችን ገቢ እንዲያድግ አግዘዋል፡፡ እንዲሁም ለአርሶ አደሮች የተሻሻሉ የአመጋገብ ውጤቶችን አስገኝተዋል፡፡
በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ለሱዳን ዳይሬክተር በበኩላቸው የኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ለጠቅላላ ምርቱ 45 ከመቶውን እንዲሁም 80 በመቶ የሚሆነውን የሰራተኛ ኃይል የሚቀጥር በመሆኑ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ወሳኝ ዘርፍ ነው ፡፡ በዘርፉ እስካሁን ድረስ አበረታች ውጤቶች የተገኙ ቢሆንም ቀሪ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና የምርታማነት ግኝቶችን ለማፋጠን ፣ ለተዛባ የአየር ንብረት ሁኔታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ፣ የመሬት መበላሸትን ለመቅረፍ እና በዘርፉ ላይ የተመረኮዘ የተፈጥሮ ሃብት መሰረትን ለማሳደግ ተጨማሪ ስራ ያስፈልጋል ብለዋል።
ይህ ተጨማሪ ፋይናንስ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እና የኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ ሙሉ አቅሙን መጠቀም እንዲችል ይረዳዋል ብለዋል። ገንዘቡ እስካሁን የተገኙ ውጤቶችን ለማሳደግ እና የተለያዩ ተጨማሪ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን ለማሳደግ የተመደበ መሆኑን ተጠቅሷል ፡፡
በተጨማሪም ገንዘቡ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የተፈጠሩትን ያልተጠበቁ የፋይናንስ ክፍተቶችን የሚሞላ እና ከፍተኛ ወጪ በመጠየቃቸው ምክንያት የዘገዩ የፕሮጀክት ሥራዎች አፈፃፀም ያፋጥናል ተብሏል፡፡
ኢፕድ ዘገባ እንዳመለከተው፣ ለሁለተኛው የግብርና ልማት ፕሮጀክት በ 167 ወረዳዎች በአማራ ፣ በኦሮሚያ ፣ በደቡብ ፣ በትግራይ ፣ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ፣ በጋምቤላ እና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ይተገበራል ፡፡ ፕሮጀክቱ በቀጥታ ለግብርና ዕድገት ከፍተኛ አቅም ባላቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ 1.6 ሚሊዮን አነስተኛ አርሶ አደሮችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል ፡፡