እነእስክንድር ነጋ አስገድደው ካላቀረቡን በቀር አንከራከርም አንቀርብም በማለት ለፍርድ ቤት ተናገሩ – ጠበቆቻችንን አሰናብተናል ብለዋል


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
የነሐሴ 6 የነእስክንድር ቤት ውሎ
ፍርድቤቱ የዛሬ ቀጠሮ አቃቢ ሕግ የአቀረበውን የሰው ምስክር ግማሾቹ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዲመሰክሩ ግማሾቹ በዝግ ችሎት እንዲ መሰክሩ ብይን ሰጥቷል።
እነእስክንድርም ፍርድቤቱ በሰጠው ውሳኔ ከዚህ በኋላ የክርክሩ አካል መሆን አንፈልግም ። ጠበቆቻችንን አሰናብተናል ብለዋል። የሁሉም ስምምነት መሆኑን ገልፀው ከችሎት ወጥተዋል።
ፍርድቤቱም ምስክሮችን በ8 እንዲቀርቡ አዟል ።እነ እስክንድርም ከዚህ በኋላ አስገድደው ካላቀረቡን በቀር አንከራከርም አንቀርብም ብለዋል።
“ክሳችን በርካታ ሰው የሞተበት የጄኖሳይድ ባህሪ ያለው ነው። ይሄ ክስ ለሚዲያ ክፍት መሆን አለበት። መስካሪዎች ማንነታቸው መታወቅ አለበት። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ በዚህ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እኛን ብቻ ሳይሆን የማች ወገኖችን ፍትህ ስለሚያዛባ በዚህ ክርክር አንሳተፍም። የፈለጋችሁት መፍረድ ትችላላችሁ። ጠበቆቻችንንም እዚሁ አሰናብተናል። ካላስገደዳችኹን በስተቀር ችሎት አንቀርብም” እስክንድር ነጋ

ዐቃቤ ህግ…ይህ የአንተ ሃሳብ ነው። ሌሎች ተከሳሾች አስተያት ይስጡ..

ስንታየኹ ቸኮልና አስቴር ስዩም…”እኛም እንደ እንደእስክንድር ነው ሃሳባችን። አቁዋማችን አንድ ዓይነት ነው”
ዳኛ “መንግስት ጠበቃ ያቆምላችኹና ይከራከርላችኅል”

እስክንድር :-ጥያቄያችን የጠበቃ ማቆምና አለማቆም ጉዳይ አይደለምን። በዚህ ችሎት ትክክለኛ ፍትህ እናገኛለን ብለን ስለማናስብ የሂደቱ አካል መሆን አንፈልግም…

ዐቃቤ ህግ..
ፖሊስ በቀጠሮአቸው ቀን እያገደደ ችሎት እንዲያመጣቸው ይታዘዝልን”
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 3 ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ሕግ የምስክሮች እና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ 699/2003ን መሠረት በማድረግ ምስክሮችን እንዲያሰማ ብይን ሰጠ።
ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በግልጽ ችሎት አይታይም በማለት የሰጠውን ብይን በመቃወም የሂደቱ አካል አንሆንም በማለት ጠበቆቻቸውን አሰናብተዋል።
ዐቃቤ ሕግ በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ክርክር የሚካሄደው በግለሰቦች ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የሕዝብ እና የመንግሥት ጥቅም እንዳይጎዳ ተጠርጣሪዎች ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ተጠብቆ በመንግሥት ተከላካይ ጠበቃ እንዲወከሉ አመልክቷል።
ችሎቱም ይህንን መነሻ በማድረግ ፍርድ ቤት ለተጠርጣሪዎች የመንግሥት ተከላካይ ጠበቃ እንዲመደብላቸው ትእዛዝ ሰጥቷል።
በአዋጁ መሠረት የዐቃቤ ምስክሮችን ለመስማት ለነሐሴ 08 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
ይህ አዋጅ በኢትዮጵያ ካለፉት 9 ዓመታት ወዲህ በስፋት እየተሠራበት ሲሆን፣ በተለይም በቅርቡ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ ጥቅም ላይ መዋሉ አይዘነጋም።