የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ፡ ከሰኞ ሰኔ 22/2012 እስከ ዛሬ ድረስ

ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ በሰው እጅ መገደሉ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ነገሮች ተከስተዋል። ግድያውን ተከትሎ በነበረ አለመረጋጋት የተነሳ ኢንተርኔት በመላ አገሪቱ ለ23 ቀናት ያህል ተቋርጧል። ከ7000 በላይ ሰዎች ታስረዋል። ከአንድ ሺህ በላይ መኖሪያና ንግድ ቤቶች በእሳት ወድመዋል። ከ167 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። የሃጫሉን ህልፈት እና ተከትሎ የተከሰቱትን አበይት ጉዳዩች መለስ ብለን ቃኝተና…