የህዳሴውን ግድብ እውን ማድረግ ካልቻልን ግብጾች ሰላም አይሰጡንም – ዶ/ር ኢ/ር ጥላሁን ኤርዱኖ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የዘላለም ታሪካችን የጦርነት የሆነው ዓባይን በጊዜ ካለመገደባችን የተነሳ ነው፤ አሁን ላይ ያንን ታሪክ ለመቀየር የሚያስችል ግድብ እየገነባን ነው – ዶ/ር ኢ/ር ጥላሁን ኤርዱኖ
Image may contain: 1 person, eyeglasses and closeup👉የህዳሴውን ግድብ ቶሎ ካልጨረስን የግብጽ ጮኸትና ማስፈራሪያ ብሎም በውስጥ ጉዳይ መግባት ነገር አይቆምም፤
👉ኢትዮጵያውያን ደግሞ ቀድሞም ከዴሞክራሲ እጥረት በስተቀር ከፍተኛ ህዝባዊ አንድነት (ህብረት) አለን፤ ለድል ሲያበቃን የነበረውም ይሄው በአንድነት መቆማችን ነው።
👉 አሁንም ህብረታችን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። አለበለዚያ አገራችን የጠላቶቻችን መፈንጭያና መጫወቻ ሜዳ መሆኗ የማይቀር ይሆናል።
👉 በኢትዮጵያ ለሚፈጠሩ ማናቸውም የሰላም እና የውስጥ ችግሮች በዓባይ ጉዳይ የተነሳ የሚመጡ ረጃጅም እጆች እንዳሉ ሊታወቅ ይገባል።
👉ዛሬ እየገደብን የሚጮሁት ጩኸት ስለግድብ ሃሳብ ባልነበረን ሰዓት ሲያደርሱብን ከነበረው ጥፋትና ውድመት ቢያንስ እንጅ እንደማይበልጥ ሊታወቅ ይገባል።
👉 የህዳሴውን ግድብ እውን ማድረግ ካልቻልን ሰላም አይሰጡንም፤ በቀበሌ ተሸንሽነን ስናበቃም ፍየል እንኳን ውሃ እንዳይጠጣ ማድረግ ነው የሚፈልጉት።አጀንዳቸው ይህ ነው።
👉 የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጎሳ፣ በአካባቢና በመንደር ሳይከፋፈል ወደ ህብረቱ መምጣትና ግድቡን መጨረስ አለበት።
👉የኢትዮጵያ መንግሥት በምንም መልኩ የመጪውን ትውልድ እጣ ፈንታ ጉዳይ በሚመለከት ነገር ምንም አይነት ድርድር ውስጥ መግባት የለበትም። የኢትዮጵያ ህዝብም ያለው አማራጭ ግድቡን ገንብቶ አገሩን ይዞ በሰላም መኖር ነው።
👉ግብጾች ካላበዱ በስተቀር ጦርነት ያደርጋሉ ብዬ አላስብም። ምክንያቱም በምንም ተዓምር በጦርነት አሸናፊም ተጠቃሚም መሆን አይችሉምና ።
👉 የኢትዮጵያ የጦርነት ታሪክና ዝግጅት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ኢትዮጵያ ጦር ማዝመት ሳይጠበቅባት ምንጮቿን በመዝጋትና በማድረቅ እንዳይዋጉ ማድረግ ለእሷ ቀላል ነው።
👉 የግብጽ የጦር ነጋሪት ጎሳሚዎች ይሄን ህልም ትተው የግብጽን ህዝብ የወደፊት ተስፋ ማሰብ ይኖርባቸዋል።
👉 ኢትዮጵያ የማንንም መብት ስለማትነካ ማንም ሲያስፈራራት በቀላሉ የምትደነግጥ አገር አይደለችም፤ ደንግጣም አታውቅም።
👉 የኢትዮጵያን ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም መርህን ግብጽም፣ ጦርነት ያወጁት ባለሃብትም በሚገባ የሚገነዘቡት እውነታ ነው። እንዋጋ ካሉም እንደተለመደው ውጤታቸው ተሸንፎ መሄድ ነው፤ ይሄንንም ከፉከራቸው ባለፈ ያለ እውነት መሆኑን ያውቁታል።
👉 ዋናው ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት አሁን ላይ በደንብ ነቅተው መጠበቅ መቻል አለባቸው። ስለዚህ ናፖሊዮን ቦናፓርት እንዳለው “ሰላምን አጥብቀህ የምትሻት ከሆነ ለጦርነት ተዘጋጅ” ነውና አባባሉ።
👉 በዓባይ ላይ አንድ ህዳሴን ብቻ ሳይሆን ሌሎች የህዳሴን አይነት ግድቦችን እውን ማድረግ፤ ውሃው ተርባይኖችን መትቶ እነርሱ ጋ ይደርሳል። ይህ ሲሆን የግብጽ ጩኸት ምክንያት ያጣል፤
👉 የዓለም ከፍተኛ ምሑራን ከግብጽ ጋር ወዳጅነት ያላቸው የእነ እንግሊዝ ምሑራን ጭምር ይሄንኑ የሚያጠናክር አያሌ ጥናታዊ ጽሑፎች ማቅረብ ይቻላል።
👉 ለምሳሌ አንደርሰን የተባሉ ጸሐፊ፣ የኢትዮጵያ ወንዞች ተገድበው ለኃይል ማመንጫነት ከማዋል ሌላ ለኢትዮጵያ የሚጠቅሙት ነገር እንደሌለ ያስረዱት።
👉 ኢትዮጵያ ይሄን ሀብቷን ገድባ ለልማቷ ማዋል፤ በዛውም እነሱን ውሃ እንደማታሳጣ ማሳየት መቻል አለባት። ይሄን ደግሞ እናደርገዋለን።
👉የህዳሴውን ግድብ መገንባት ብቻ ሳይሆን ህይወት ኖሮት ለረጅም ጊዜ መጠቀም የምንችለው የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ስናጠናክር እና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተለይ በግብርና የሚተዳደረው ሰፊው ህዝብ በያለበት አካባቢ አንዲት ማንኪያ አፈር ወደየትም እንዳትሄድ በቁጥጥሩ ሥር ማድረግ መቻል አለበት።
👉ግብጾች ብክነት የተሞላበትን የውሃ አጠቃቀም ስርዓታቸውን ማረም ይኖርባቸዋል። በተለይም ኋላ ቀርና ውሃ አባካኝ የሆነውን የግብርና ስርዓታቸውን ማረም፤ የውሃ ፍጆታቸው አነስተኛ የሆኑ የግብርና ምርቶችን በአማራጭ መያዝ ይኖርባቸዋል።
👉 የአረብ ሊግ አባል አገራትም የሁለቱን አገር ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የሁሉንም አገር ህዝቦች አኩል ማየት አለባቸው። ካልሆነ ባለው እሳት ላይ ቤንዚን እየጨመሩ እሳቱ እንዳይዳፈን ከማድረግ የዘለለ ተግባር አይኖራቸውም።
👉 ሃይልና ገንዘብ አለን ብለው በዚህ ላይ ጣልቃ መግባት የሚፈልጉ ድርጅቶችና አካላት ካሉ እነርሱ ሞራል የሌላቸው ከመሆናቸውም በላይ በጉልበት የሚያምኑ ናቸው፤ በዚህ መንገድ ደግሞ ዘላቂ ውጤት አይመጣም።
ምንጭ አዲስ ዘመን ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም