በመስቀል አደባባይ የሰኔ 16/2010 ሰልፍ ላይ ጥቃት ያደረሰችው ኬንያ ውስጥ አለች የተባለችው ሴት አልተያዘችም ተባለ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


– ከአገር ውጪ ኬንያ ውስጥ አለች የተባለችውን ሴት መያዝ አንዱ አስፈላጊ ነገር እንደሆነ ኃላፊው ተናግረዋል።

– ከሰኔ 16ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ?

BBC Amharic ልክ የዛሬ ሁለት ዓመት ሰኔ 16/2010 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ድጋፍ በመስቀል አደባባይ በተጠራው ሰልፍ ላይ በተሰነዘረው የቦንብ ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

ጥቃቱን በማቀነባበርና በመምራት አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ክስ የተመሰረተ ሲሆን ሁለት ሰዎች ደግሞ አለመያዛቸውን በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ፍቃዱ ጸጋ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

Photo File - Meskel Square

Photo File – Meskel Square

አምስቱ ግለሰቦች ላይ የቀረበው ክስ የሽብር ድርጊት የሚል ሲሆን የፀረ ሽብር አዋጁ 652/2001 አንቀጽ 3 ስር መከሰሳቸውን አብራርተዋል።

የሰኔ 16 ተከሳሾች መዝገብ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት ተከሳሾች የመጨረሻ ይቅረብል ያሉት ሰነድ እንደነበር የሚያስታውሱት አቶ ፍቃዱ፣ እርሱ ላይ ብያኔ ለመስጠትና የፍርድ ውሳኔውን ለማዘጋጀት እን ሌሎች የሚያስፈልጉ ነገሮች መኖራቸውን ለመወሰን ቀጠሮ ተሰጥቶ እንደነበር ገልጸዋል።

ከኮሮናወረርሽኝ ወዲህ ችሎቶች ሥራ በማቋረጣቸው የተከሳሾች ጉዳይ አለመንቀሳቀሱን አቶ ፈቃዱ ጸጋ አመልክተዋል።

ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩት አምስቱም ተከሳሾች ይከላከሉ ተብሏል ያሉት አቶ ፍቃዱ፣ እነርሱም መከላከያ ምስክር የሚሉትን አሰምተዋል ሲሉ ገአስታወስኣል።

“ነገር ግን በምስክርነት የጠቀሷቸው አንዳንድ ስልጣን ላይ የነበሩ ሰዎችን የመከላከያ ምስክሮቻችን ናቸው በሚል ስለጠየቁ፣ በወቅቱ መገናኛ ብዙሃን ላይ ቀርበው ስለተናገሩ ብቻ፣ ፍርድ ቤቱ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አለው ወይስ የለውም ተገቢ ነው፣ አይደለም የሚለውን ለመወሰን ቀጠሮ ሰጥቶ በነበረበት ወቅት ነው ወረርሽኙ ተከስቶ ችሎቱ የተቋረጠው።”

ነገር ግን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አቃቤ ሕግ ማስረጃ የማሰማት ሂደት ማለቁን ጨምረው ተናግረዋል።

በቁጥጥር ስላልዋሉት ሁለት ሰዎች ሲናገሩም አንደኛው የቀድሞ የደኅንነት ኃላፊ የነበሩትና ሌላኛዋ ይህንን ጉዳይ አቀናብራለች የተባለች ሴት በክሱ ላይ ተጠቅሰው ያልተያዙ መሆናቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የቀድሞ የደኅንነት ኃላፊ በሌላ መዝገብም መከሰሳቸውን በማስታወስ፣ ክስ የቀረበባቸውና በፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋሉት አምስቱ ሰዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በአቃቤ ሕግ የቀረበባቸው ክስ ስለተረጋገጠ ተከላከሉ ተብሏል።

ሁለቱ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎችን ለመያዝ ምን እየተደረገ ነው ተብለው የተጠየቁት አቶ ፍቃዱ፣ ምርመራ አይቆምም ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

ማስረጃዎች በተገኙና በተረጋገጡ ልክ ሂደቱ ይቀጥላል። በወቅቱ በቂ ጥርጣሬ የሚያጭሩ ነገሮች ነበሩ። በሌላ ወንጀል የተጠረጠረ ሰው በዚህ ጉዳይ ማስረጃ መሆን እችላለሁ ብሎ ቃሉን የሰጠ ሰው ነበር ሲሉም አክለዋል።

“እርሱን በሌላ ጉዳይ ላይ ተጠርጣሪ ማድረግ ነው የሚሻለው ወይስ እዚህ ጉዳይ ላይ ምስክር ማድረግ ነው የሚሻለው የሚለውን መወሰን የሚፈልግ ነገር ሊሆን ይችላል” ሲሉም ያለውን ሁኔታ ያስረዳሉ።

ግን ያልተያዙትን ሰዎች ወደ ሕግ የማቅረቡ ጥረት እንደሚቀጥል በተለይም ከአገር ውጪ ኬንያ ውስጥ አለች የተባለችውን ሴት መያዝ አንዱ አስፈላጊ ነገር እንደሆነ ኃላፊው ተናግረዋል።