የግድቡን ሙሌት በተያዘለት እቅድ በማከናወን በቀጣይ አመት ኃይል ማመንጨት እንጀምራለን

የግብጽ ተለዋዋጭ አቋም ኢ- ፍትሃዊ ፤ የኢትዮጵያን ፍትሃዊና ተፈጥሯዊ ሃብቷን የመጠቀም መብት የጣሰ ነው

DW : በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ በሦስቱ የተፋሰሱ ሀገራት መካከል አልደረስ ያለው ስምምነት መሰረታዊ ጉዳይ የወደፊት የውኃ አለቃቀቅ እና አጠቃቀም ነው ሲሉ አንድ የግድቡ ተደራዳሪ ተናገሩ። በጉዳዩ ላይ ዛሬ በተደረገ የምሁራን ውይይት ላይ እንደተገለጸው የግብጽ ተለዋዋጭ አቋም ኢፍትሃዊ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያን በሃብቷ የመጠቀም ፍትሃዊና ተፈጥሯዊ መብት የጣሰ ነው ተብሏል። ግድቡን የምንሞላው የራሳችንን የውኃ ድርሻ በመጠቀም በመሆኑ የግድቡን ሙሌት በተያዘለት እቅድ በማከናወን በቀጣይ አመት ኃይል ማመንጨት እንጀምራለን፣ ምሁራኑም የደረጃቸውን ልክ የሚወጡበት ጊዜ አሁን ነው ተብላል። DW

——————–