በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3203 ደረሰ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ ዘጠና ስምንት (98) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ በከተማው ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሶስት (3203) ደርሷል፡፡ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በከተማው በተደረጉ የአስከሬን ምርመራዎች አንድ (1) ሰው በበሽታው ሕይወቱ አልፏል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት ሰባ ዘጠኝ (79) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል፡፡