አስር የደቡብ ሱዳን ሚኒስትሮች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፡፡

የደቡብ ሱዳን 10 ሚኒስትሮች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ሚካኤል ማኩይ ተናገሩ፡፡በእርግጥ የሕመም ምልክት አላሳዩም እንጅ መግለጫውን የሰጡት የሚኒስትሩ ቃል አቀባይም ራሳቸውም ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ሚኒስትሮቹ ለኮሮና ቫይረስ የተጋለጡት ከቀድሞው ከፍተኛ የኮሮና መከላከል ግብረ ኃይል አባላት ጋር ንክኪ ስለነበራቸው እንደሆነ ተገልጧል፡፡

ከግብረ ኃይሉ አባላት የጤና ሚኒስትሩ ብቻ ናቸው ቫይረሱ ያልተገኘባቸው፡፡ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ሚኒስትሮቹ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሆኑና በየራሳቸው ልዩ ማቆያ እንደሚገኙም የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ የግብረ ኃይሉ አባል የነበሩት ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የሚወራውን ግን አስተባብለዋል፡፡
ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር (ዶክተር)፣ ባለቤታቸው እና ጠባቂያቸው ግን ቫይረሱ ቀደም ብሎ እንደተገኘባቸው አስታውቀዋል፡፡ የማቻር ቃል አቀባይ በራሳቸው ለይቶ ማቆያ እንደሚገኙም ተመላክቷል፡፡ የጤና ሥርዓቷ በወረርሽኙ እየተፈተነባት ያለችው ደቡብ ሱዳን እስከዛሬ 481 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጣለች፡፡

 መረጃ ቲቪን በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት እንድናቀርብ እገዛችሁን እንሻለን።
መረጃ ቲቪን ለማገዝ ይህን ሊንክ በመጫን አባል ይህኑ - JOIN Mereja TV