አዲስ አበባ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ደረሰ በተባለው ወረርሽኙ መዛመት ምን ያህል እስረኞች ሰለባ እንደ ሆኑ በውል አላውቅም

DW : አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ ፖሊስ ጣቢያ በአንድ ግለሰብ ምክንያት ሳይገባ እንዳልቀረ በተጠረጠረ በህግ ጥላ ስር የነበሩ 40 ተጠርጣሪ እስረኞችን ጨምሮ 66 ሰዎች በኮሮና ተሕዋሲ መያዛቸውን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ትናንት አስታውቀዋል። መንግሥት የኮሮና ወረርሽን ያሳደረውን ስጋት ተከትሎ ቀደም ሲል በርካታ የህግ ታራሚዎችን እስከመልቀቅ እርምጃ ወስዶ ነበር ። ነገር ግን የተሰጋው አልቀረም ። የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ደረሰ በተባለው ወረርሽኙ መዛመት ምን ያህል እስረኞች ሰለባ እንደ ሆኑ በውል አላውቅም ብሏል። በማረሚያ ቤቶችም ሆነ በየ ፖሊስ ጣቢያው በሚገኙ ማረፊያ ቤቶች የታራሚዎችን አያያዝ በተመለከተ የሚከታተል አንድ የባለሞያዎች ቡድን ማቋቋሙን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ተናግረዋል።

https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/6CBE0998_2.mp3መረጃ ቲቪን በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት እንድናቀርብ እገዛችሁን እንሻለን።
መረጃ ቲቪን ለማገዝ ይህን ሊንክ በመጫን አባል ይህኑ - JOIN Mereja TV