ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ መጨናነቅ በሚታይባቸው አካባቢዎች በመዘዋወር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ግንዛቤ እየሰጡ ነው

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

ኢ/ር ታከለ በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ግንዛቤ እየሰጡ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ ከተማ መጨናነቅ በሚታይባቸው አካባቢዎች በመዘዋወር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚደረጉ ጥንቃቄዎች ዙሪያ ምልከታ እያደረጉ ነው።
በዚህ መሰረትም በመርካቶ፣ አትክልት ተራና መገናኛ አካባቢዎች መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች በተለይም በሰዎች መካከል መጠበቅ ስላለባቸው ርቀቶች ግንዛቤ በመስጠት ላይ መሆናቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
(ኤፍ ቢ ሲ) (ከታች ምስሎቹን ይመልከቱ)