በአዲስ አበባ በሚገኙ 13 ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህሲ መድሃኒት ርጭት ሊካሄድ ነው

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህሲ መድሃት ርጭት ሊካሄድ ነው
Walta : በአዲስ አበባ በሚገኙ 13 ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህሲ መድሃኒት ርጭት እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ የመንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሞገስ ጥበቡ ለአዲስ ቲቪ በሰጡት መግለጫ በነገው ዕለት በከተማዋ ዋና ዋና ተብለው በተለዩ 13 መንገዶች ላይ ዲስኢንፌክት የማድረግ ስራ ይከናወናል።
በዚህም መሠረት 41 ኪሎ ሜትር የሚሽፍኑት ተከታዮቹ መንገዶች የፀረ ተዋህሲ መድሃኒቶች ርጭት ይካሄድባቸዋል፡-
– ከመስቀል አደባባይ – ቦሌ ፣
– ከመስቀል አደባባይ – ጦር ሃይሎች ፣
– ከመስቀል አደባባይ – 6 ኪሎ ፣
– ከመስቀል አደባባይ – ጎተራ – ሳሪስ
– ከመስቀል አደባባይ – መገናኛ ፣
– ከብሄራዊ – ሜክሲኮ፣
– ከሱፐር ማርኬት – ካዛንችስ – ኡራዔል ፣
– ከምኒልክ አደባባይ – አምባሳደር – መስቀል አደባባይ፣
– ከምኒልክ አደባባይ – ፓስተር፣
– ከምኒልክ አደባባይ – 4 ኪሎ – መገናኛ፣
– ከምኒልክ አደባባይ – 6 ኪሎ ፣
– ከምኒልክ አደባባይ – አውቶብስ ተራ ፣
– ከምኒልክ አደባባይ – ተክለሃይማኖት
በዚህ ስራ ሳቢያም የተጠቀሱት መንገዶች ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ለአገልግሎት ዝግ እንደሚሆኑም ኢ/ር ሞገስ አስታውቀዋል፡፡