ዳር ያልደረሰ ምርምር ልክ እንደተጠናቀቀና ወደ ምርት እንደሚገባ አስመስሎ መናገሩ ጥፋት ነው።

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

እንደ ዜጋ በመንግስት ስም በሕዝብ ላይ የሚረጩ አዘናጊና ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎችን ልንቃወምና ልናከሽፍ ይገባል።
አትጨባበጥ የተባለውን ሕዝብ ሲያጨባብጥ የዋለው የመንግስት ባለስልጣናት ውዥንብር መፍጠርና ድንቁርና አንድ ሊባል ይገባል።
ለኮሮና መድሐኒት ተገኝቷልና የምርምር ሒደቱ ተጠናቆ ወደ ምርት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ነው መግለጫ ልሰጥ ነው ሲሉ የመንግስት ባለስልጣናት ለሚዲያ መናገራቸው ምን ያህል ለዜጎች ደሕንነት ንዝሕላል እንደሆኑ ያሳያል።
የመንግስት ባለስልጣናትን መግለጫ ተከትሎ አትጨባበጥ ሲባል የከረመው ሕዝብ በመተቃቀፍ ሲደሰት ዋለ። የመድኋኒት ምርምርና ግኝት አስቸጋሪና ጊዜ የሚወስድ ወሬው ሁሉ ባዶ ነው።ዳር ያልደረሰ ምርምር ልክ እንደተጠናቀቀና ወደ ምርት እንደሚገባ አስመስሎ መንግስት መናገሩ ጥፋት ነው። የመንግስት ባለስልጣናት ድንቁርና አንድ ሊባል ይገባል።
እንደ ዜጋ በመንግስት ስም በሕዝብ ላይ የሚረጩ አዘናጊና ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎችን ልንቃወምና ልናከሽፍ ይገባል። የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመዋጋት ራሳችንና ሕብረተሰቡን ከበሽታው ለመታደግ የጠሰተንን የጤና መመሪያዎች በመተግበር ከቤት ባለመውጣት እና ንፅሕናችንን በመጠበቅ ልንተገብረው ይገባል። አንዘናጋ። የባሕል መድሐኒት ተገኘ ብለን አንዘናጋ። ገና ምርምር ላይ ስለሆነ ጊዜ ይወስዳል ሲል መንግስት አሳውቋል። ስለዚህ ሳንዘናጋ ከኮሮና ቫይረስ ራሳችንን እንጠብቅ። ኮሮናን በጋራ እንከላከል። አንዘናጋ ።#MinilikSalsawi