የቡድን 20 አባል አገራት ለደሃ አገራት የሰጡትን ብድር ይሰርዙ ሲሉ የአለም ባንክ እና የአለም የገንዘብ ተቋም ጠየቁ

Joint Statement World Bank Group and IMF Call to Action on Debt of IDA Countries

የአለም ባንክ እና የአለም የገንዘብ ተቋም የደሃ አገራት እዳ እፎይታ እንዲደረግ ጠየቁ ሁለቱ አለምአቀፍ የገንዘብ እሮብ ምሽት ባወጡት የጋራ መግለጫ የቡድን 20 አባል አገራት ለደሃ አገራት የሰጡትን ብድር ይሰርዙ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡በጋራ መግለጫቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከአለም ህዝብ እሩቡን በያዙት አገራት የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ የአደጋ ስጋት ደቅኗል ያሉት ተቋማቱ አበዳሪ ሃብታም አገራት ለድሃ አገራት የሰጡትን ብድር ክፍያ ከመቀበል ይቆጠቡ ብለዋል፡፡

The World Bank Group and International Monetary Fund have issued the following joint statement to the G20 concerning debt relief for the poorest countries: The coronavirus outbreak is likely to have severe economic and social consequences for IDA countries, home to a quarter of the world’s population and two-thirds of the world’s population living in extreme poverty.
የብድር ክፍያ መቋረጡ የሚገኘው ገንዘብ ድሆቹ አገራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለተጋረጠባቸው እክል መቀልበሻ ሁነኛ አማራጭ ነው ያለው የጋራ መግለጫው፡፡ በተጨማሪም ቀውሱ የሚያደርሰውን ተፅእኖ እና የገንዘብ ፍለጎት ለመገምገም ግዜ ይሰጣል ብሏል፡፡ በተቋማቱ ለካፒታል የተላከው የጋራ መግለጫ የቡድን 20 አገራት ሁለቱን የገንዘብ ተቋማትን የየአገራቱን የብድር ሁኔታ በመተንተን እና በማደራጀት እንዲሁም የተጋረጠውን ችግር ከመፍታት አንፃር የተቀናጀ እርምጃ ሊወሰድበት የሚችለውን አማራጭ ሃሳብ በማቅረብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠቋል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ማክሰኞ መጋቢት 14 ለቡድን 20 አገራት በፃፉት ደብዳቤ የአፍሪካ አገራት ለተጋረጠባቸው አደጋ የእዳ ስረዛን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎችን እንዲያደርጉ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡