“ጤናችን ይጠበቃል፤ ግድባችን ይጠናቀቃል!” በሚል ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ የቦንድ ሳምንት ይፋ ሆኗል፡፡


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
Walta : የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መሰረት ድንጋይ የተቀመጠበትን ዕለት ከወቅታዊው የኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር በማስተሳሰር “ጤናችን ይጠበቃል፤ ግድባችን ይጠናቀቃል!” በሚል መሪ ቃል ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ፍጻሜ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የቦንድ ሽያጭ ሳምንት ይፋ ማድረጉን የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቋል፡፡
በዚህ መርሃ ግብር 500 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ እቅድ መያዙንም የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ሮማን ገብረስላሴ ገልጸዋል፡፡የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንትና የጽህፈት ቤቱ አባል ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ በበኩላቸው ለግድቡ ፍጻሜ የህብረተሰቡ ድጋፍ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የቦንድ ሽያጭ ሳምንት ይፋ በተደረገበት ስነስርአት የዋሪት ሙሉ ጥላ ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር 1 ሚሊየን ብር በስጦታ አበርክቷል፡፡
የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ ትህትና ለገሰ የግድቡን ግንባታ ከግብ ማድረስ የሚቻለው የህብረተሰቡ ጤና ሲጠበቅ መሆኑን ገልጸው፣ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለሚደረገው ጥረት ለጤና ሚኒስቴር በተመሳሳይ የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ስለመሆናቸው ተናግረዋል፡፡የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመግታት ህብረተሰቡ የጤና ባለሙያዎችን ምክር መተግበር እንደሚገባው በመድረኩ ተገልጿል፡፡የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መሰረት ድንጋይ የተቀመጠበት 9ኛ ዓመት መጋቢት መጋቢት 24 ታስቦ ይውላል፡፡