የአማራ ክልል ባለስልጣናትን ማመን ቀብሮ ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአማራ ክልል ባለስልጣናትን ማመን ቀብሮ ነው።
ከአማራ ክልል የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ሕዝቡን ሆን ብሎ በሁለት መንገድ ለመግደልና ለማሰር በክልሉ ባለስልጣናት ዘመቻ ተጀምሯል። የተረፈውን የክልሉን ሕዝብ ደግሞ ሞራሉን በመግደል ለማዳከም የታቀደ ይመስላል።
በአማራ ክልል ባለስልጣናቱ በኮሮኖ ቫይረስ ዙሪያ ራሳቸዉ ያወጡትን ደንብ እየጣሱ መሆናቸዉን ነዋሪዎች ለጀርመን ድምጽ ተናግረዋል።ይህ ማለት ደግሞ እጅግ አደገኛና የሕዝብን ሕይወት በጅምላ ለማጥፋት ሆን ተብሎ የታቀደ ሴራ እንዳለ ከበቂ በላይ ጠቋሚ መረጃ ነው።
ሌላኛውና ሁለተኛው ደግሞ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ያወጣው መግለጫ ነው። የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል እንደሚባለው ከሕወሓት በወረሰው የሴራና የተንኮል ፖለቲካ ልምድ የተቃኘ የጠለፋ እና የፍጅት መግለጫ አውጥቷል።
የከተማው አስተዳደር መረጃ ሕግ ለማስከበር ሳይሆን ንጹሃንን ለመጥለፍ ሆን ተብሎ የሚጀመር ዘመቻ እንዳለ ሌላኛው ጠቋሚ መረጃ ነው። የክልሉን ባለስልጣናት ማመን ቀብሮ ነው። ሕዝቡ የግፋቸው ግፍ ጣራ ከነካ ባለስልጣናት ተንኮልና ሴራ ራሱን ሊጠብቅ ይገባል። #MinilikSalsawi