" /> በራሳችሁ ወጪ ለ14 ቀናት ሆቴል ትቆያላችሁ የተባሉ ኢትዮጵያውያን የምንከፍለው ገንዘብ የለንም ብንልም የሚሰማን አጥተናል ይላሉ። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

በራሳችሁ ወጪ ለ14 ቀናት ሆቴል ትቆያላችሁ የተባሉ ኢትዮጵያውያን የምንከፍለው ገንዘብ የለንም ብንልም የሚሰማን አጥተናል ይላሉ።

ሸገር FM : ከዱባይ እና ከሌሎችም ሀገራት አዲስ አበባ ደርሰው በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በራሳችሁ ወጪ ለ14 ቀናት ትቆያላችሁ የተባሉ ኢትዮጵያውያን፣ “የምንከፍለው ገንዘብ የለንም” ብንልም የሚሰማን አጥተናል ይላሉ። ሸገር በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የጠየቀው የአየር መንገዱ የኮምንኬሽን ክፍል፣ ጥያቄያችሁን በጽሑፍ ላኩልን ሲል መልሷል። የከተማ መሥተዳድሩ በበኩሉ፣ “መንግሥት መክፈል ለማይችሉ ከውጭ ተመላሽ ዜጎች፣ ጊዜያዊ ማቆያ (ማደርያ) እና ምግብ አሰናድቶ እየጠበቃቸው ነው፣ ኢትዮጵያውያኑ ፈፅሞ መጉላላት የለባቸውም” ሲል ለሸገር ነግሯል።

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV