ከማላዊ ወደ ሞዘምቢክ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ውስጥ ቢያንስ 64 ኢትዮጵያዊያን ሞተው ተገኙ

64 migrants found dead in truck in Mozambique

ከማላዊ ወደ ሞዘምቢክ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ውስጥ ቢያንስ 64 ኢትዮጵያዊያን በመተፋፈን ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን ባለስልጣናት አስታወቁ።ዛሬ ጠዋት በሞዛምቢክ ምዕራባዊ ግዛት በምትገኘው ቴቴ በተባለችው ክፍለሃገር ውስጥ በተገኘው ተሽከርካሪ ውስጥ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 14 ሰዎች በህይወት ተገኝተዋል።

More than 60 undocumented migrants believed to be Ethiopians have been found dead in a cargo truck in Mozambique’s northwestern Tete province.

The truck entered Mozambique from Malawi and was stopped early Tuesday at a checkpoint in Moatize, near the Zambezi River, according to Zitamar News.

“የሞዛምቢክ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ሰራተኞች የጭነት መኪናውን ሞአትዜ በተባለችው የግዛቲቱ ከተማ ውስጥ አስቁመው ሲፈትሹ ነው ሟቾቹን ያገኙት” ሲሉ የቴቴ ክፍለ ሃገር የጤና ባለስልጣን የሆኑት ካርላ ሞሴ ተናግረዋል።ባለስልጣኗ እንዳሉት በጭነት መኪናው ላይ የተሳፈሩት ሰዎች ህይወታቸው በምን ምክንያት ሊያልፍ እንደቻለ ምርመራ እየተደረገ ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያዊያኑ ህይወት ያለፈው በአየር ማጣት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምበሳደር የሆኑት አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ኢትዮጵያኑ “ከማላዊ ወደ ሞዛምቢክ ጉዞ እያደረጉ ሳለ ነው ይህ አሳዛኝ ነገር የተፈጠው ብለዋል”።አምባሳደሩ እስካሁን ባላቸው መረጃ መሠረት ኢትዮጵያውያኑ ሕይወታቸው ሊያልፍ የቻለው በኮንቴነር ውስጥ ታፍነው ነው።ከ78 ተጓዞች የ64ቱ ሕይወት ማለፉን አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።

When authorities heard bashing noises coming from inside the container, they ordered the driver to open it and they found 14 survivors inside as well as the bodies. The deceased died from a lack of oxygen, according to officials.The Mozambican driver later admitted he had been hired to smuggle the migrants from Malawi to Mozambique.The survivors will be screened for the coronavirus and quarantined, health officials told Zitamar.Mozambique is a transit route for African migrants trying to reach South Africa, one of the continent’s largest economies, according to the International Office on Migration.

Source : BBC Amharic and daily Sabah