ኢትዮጵያን ከሱዳን ጋር የሚያገናኘው መንገድ መዘጋቱ ተነገረ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኢትዮጵያን ከሱዳን ጋር የሚያገናኘው መንገድ መተማ ዮሃንስ ላይ ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ መዘጋቱን የአከባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ::

ከብቶቻችን በሱዳን የመከላከያ ሠራዊት ተወሰደብን ያሉ የመተማ ዮሃንስ ነዋሪዎች መንገዱን መዝጋታቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል::

ወደ ሁለቱም አቅጣጫዎች ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡና እንዳይወጡ መንገዱ መዝጋቱን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አንድ የአካባቢው የአማራ ክልል የፖሊስ አባል ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት “በድንበሩ አካባቢ የሁለቱም ህዝቦች ይወጣሉ ይገባሉ። ትናንትም በርካታ ከብቶች ድንበር አካባቢ ነበሩ።

እነዚህን ከብቶችም የሱዳን የመከላከያ ሠራዊት አባላት በመኪና ጭነው ወሰደቸዋል” ብለዋል።
እንደ የፖሊስ አባሉ ገለጻ ከሆነ እስከ 150 ከብቶች ለመውሰድ ሙከራ ተደርጎ ቢያንስ ከ80 ያላነሱ ተወስደዋል::

ከብቶቹን ለማስመለስ ሙከራ ቢደረግም “እናንተም የኛን ስትወስዱ ኖራችኋል እኛም አንመልስም” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።

ስለጉዳዩ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የመተማ ዮሃንስ ተወካይ ከንቲባ መንገድ መዘጋቱን እና የተዘረፋ ከብቶች መኖራቸውን አረጋግጠው መፍትሄው ምን መሆን እንዳለበት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየመከሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ቢቢሲ