ገዥው ፓርቲ ድርጅታዊ ስራዎቹን ከመንግስት መዋቅር ውጪ እንዲያካሂድ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አሳሰበ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ፓርቲ እና መንግስት ይለዩ!!
የካቲት 5፣ 2012 አዲስ አበባ::

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ገዥው ፓርቲ ድርጅታዊ ስራዎቹን ከመንግስት መዋቅር ውጪ እንዲያካሂድና ከባለሀብቶች ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከመንግስት መዋቅር ውጪ በፓርቲው አደረጃጀት ስር ብቻ እና ብቻ እንዲያካሂድ ጥሪ አቀረበ፡፡

በተመሳሳይ ፓርቲው በፌደራል እና በክልል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከሚሰሩ አባላቱ የሚሰበስበውን የአባልነት መዋጮ ከመንግስት መዋቅር ውጪ በፓርቲው ጽ/ቤቶች እና አደረጃጀት እንዲያከናውን ያሳሰበ ሲሆን፣ የመንግስት መዋቅርን በመጠቀም የሚደረግ እንቅስቃሴ የፖለቲካ ሜዳውን ያልተስተካከለ የሚያደርግ እና የተፎካካሪ ፓርቲዎችን የፖለቲካ እንቅስቃሴ አሉታዊ በሆነ መንገድ የሚጎዳ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የመግለጫውን ሙሉ መልእክት አባሪ ከተደረገው ሰነድ ይመልከቱ፡፡

Image may contain: text