በሐረር ከተማ በጥምቀት በዓል ከዋዜማው እለት ጀምሮ የደረሱ ጉዳቶች


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በሐረር ከተማ በጥምቀት በዓል ከዋዜማው እለት ጀምሮ የደረሱ ጉዳቶች (እስከአሁን በተጨባጭ የታወቁ)
(ጥር 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ከተሰጠ መግለጫ የተወሰደ)

. በከተማዋ ልዩ ስሙ መጠለያ ከሚባለው አካባቢና አቅራቢያው 224 ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለው ንብረታቸው ተዘርፏል፡፡ ከመንግስት ምንም ድጋፍ ሳይደረገላቸወ ቆይቶ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከፊሎቹ በቀይ መስቀል በኩል ብርድ ልብስ እና የምግብ ድጋፍ አግኝተው በ27-05-2012 ዓ.ም. ከነስጋታቸው ወደ ሰፈራቸው ተመልሰዋል፡፡

. በጥይት ተመተው የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር 8 ሲሆን፤ ከ6 በላይ የሚሆኑትም በድንጋይ ተመተው ቆስለዋል፡፡
. ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ታፍሰው ታስረዋል፡፡
. አንድ ቪላ ቤት ከነሙሉ እቃው ሙሉ ለሙሉ ወድሟል፡፡
. አንድ የእህል መጋዘን፣ አንድ የለስላሳ ማከፋፈያ እና አንድ ወፍጮቤት በእሳት ወድሟል፡፡
. ከ10 በላይ ሆቴሎችና ግሮሰሪዎች እንዲሁም ሱቆች በመዝረፍና በመሰባበር ወድመዋል፡፡
. በእሳት የተቃጠሉ 3 ባጃጆች እና አንድ መኪና ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል፡፡
. ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ባጃጆችና መኪናዎች ተሰባብረዋል፡፡
. ቁጥራቸው ያልታወቀ ባጃጆች ተዘርፈው ተወስደዋል፡፡
. የተዘረፉትን ባጃጆች ሳይጨምር ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ጠፍቷል፡፡
(የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረስብከት ጽ/ቤት)