የ2012 የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ እና ክልል አቀፍ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ተደረገ

የ2012 የትምህርት ዘመን የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ይፋ አድርጓል።

በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 24 እስከ ግንቦት 27/2012 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ሲሆን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ደግሞ ከሰኔ 01 እስከ ሰኔ 03/2012 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሰዓት ቢጀመሩም ነገር ግን የተለያየ የማጠናቀቂያ ሰዓት በነበራቸው ፈተናዎች በአፈጻጸም ላይ ችግር ሲፈጠር መቆየቱን የገለፀው ኤጀንሲው መፍትሔ ለመስጠት ሲባል ተመሳሳይ ሰዓት ያላቸው ፈተናዎች በተመሳሳይ ሰዓት እንዲሰጡ ተወስኗል፡፡

በዚህም መሠረት ኬሚስትሪ እና ኢኮኖሚክስ፣ ባዮሎጂ እና ታሪክ በተመሳሳይ ሰዓት እንዲሰጡ መወሰኑን ከአገር ሀቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ኢዜአ)