" /> በመፈንቅለ መንግስት ሰበብ የታሰሩት የአማራ ክልል ባለስልጣናት ከፀጥታ ተቋሙ ውጭ በሆኑ ተቋማት መመደባቸው ተሰማ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

በመፈንቅለ መንግስት ሰበብ የታሰሩት የአማራ ክልል ባለስልጣናት ከፀጥታ ተቋሙ ውጭ በሆኑ ተቋማት መመደባቸው ተሰማ

የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አዛዥ የነበረው ጀነራል ተፈራ ማሞ የአማራ ውሃ ስራዎች ኬንስትራክሽን አመራር ተደርጎ መመደቡ ታወቀ።

ከጀነራል ተፈራ በተጨማሪ የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ አመራር የነበሩት ኮሎኔል አለበልና ኮሎኔል ባምላኩም ከፀጥታ ተቋሙ ውጭ በሆኑ ተቋማት መመደባቸው ታውቋል።

ኮሎኔል አለበል አማረ የመንገዶች ባለስልጣን አማካሪ ሆኖ መሾሙን የሚያመለከቱ መረጃዎችም እየወጡ ይገኛል።

አስተያየት ሰጪዎች ቀድሞውኑ ባለስልጣናቱ የታሰሩት ሆን ተብሎ ካሉበት ስልጣን ለማውረድና ከጸጥታ ተቋማቱ ለማራቅ የተሰራ የፖለቲካ ሴራ ነው ይላሉ።


የመረጃ ቲቪ አባል ይሁኑ - JOIN US