የአገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት የምርጫ 2012 ፈተና ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠ/ም ዐቢይ ተናገሩ።

DW : በዚህ አመት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ምርጫ የአገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት ፈተና ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

ምርጫው በመጪው ግንቦት አሊያም ሰኔ ወር ሊካሔድ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በደቡብ አፍሪካ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ምኒስትሩ ከፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ሆነው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ «በርካታ ፈተናዎች ሊኖሩ ይችላሉ» ያሉት ዐቢይ ሎጂስቲክስ፣ ሰላም እና መረጋጋትን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።

«ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫውን በጊዜ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ቢያኪያሒዱ ጥሩ ነው» ብለዋል።ዐቢይ «የጊዜ ሰሌዳው በግንቦት ይሁን በሰኔ እርግጠኛ አይደለሁም። ምክንያቱም የጊዜ ሰሌዳው የሚወሰነው በምርጫ ቦርድ ነው። በዚህ አመት ምርጫ እናካሒዳለን ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታ ነው» ሲሉ አክለዋል።

Image may contain: 2 people, people smiling, people standing