ህወሓት፣ ባይቶና እና ሳልሳይ ወያነ አረናንና ሌሎች የትግራይ ፓርቲዎችን ያላካተተ ፎረም መሰረቱ

DW : በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ተቋማት፣ የሙያ ማሕበራትና ሌሎች ድርጅቶችን ያቀፈ «የትግራይ ፓርቲዎችና ማሕበራት ፎረም» የተሰኘ የዉይይት መድረክ ተመሰረተ፡፡ በትግራይ ‘የጋራ አጀንዳዎች ‘ ላይ ይሰራል የተባለው መድረክ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ 16 ማሕበራትን ያቀፈ ነው፡፡ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣- የትግራይ ገዢ ፓርቲ ህወሓት፣ተቃዋሚዎቹ ባይቶና እና ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የስብስቡ አባላት ሲሆኑ ዓረና ትግራይ፣ የትግራይ ዴሞክራስያዊ ፓርቲና ዓሲንባ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ግን አልተካተቱም።