አሜሪካ ከኢራን ጋር ያለቅድመ ሁኔታ እደራደራለሁ አለች፡፡

Iran crisis: US ‘ready for serious negotiations’ with Tehran

አሜሪካ ከኢራን ጋር ያለቅድመ ሁኔታ እደራደራለሁ አለች፡፡

አሜሪካና ኢራን ከሰሞኑ ወደ ለየለት የጦርነት ጫፍ የደረሱ መስለዋል፡፡ አሜሪካ የኢራንን ከፍተኛ የጦር መኮንን ገደለች፤ ኢራንም በአጻፋ በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ሠፈር ላይ የሚሳኤል ድብደባ ፈጸመች፡፡ ይህንን ተከትሎ ሁለቱ ኑክሊዬር ታጣቂዎችና ደጋፊዎቻቸው ወደለዬለት ጦርነት እንዳይገቡ ዓለም ጭንቀት ውስጥ ገብታለች፡፡

The US says it is “ready to engage without preconditions in serious negotiations” with Iran following the countries’ exchange of hostilities.In a letter to the UN, the US justified the killing of Iranian General Qasem Soleimani as an act of self-defence.Iran has retaliated by firing missiles at air bases housing US forces in Iraq causing no casualties. It also told the UN it was an act of self-defence.Gen Soleimani was widely held as being Iran’s second most senior official. As head of the Revolutionary Guards’ elite Quds Force, he was an architect of Iranian policy in the region.

የኢራንን አጸፋ ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ በማኅበራዊ ገጻቸው ‹‹ሁሉም ነገር ደኅና ነው፤ ስሁኔታው ነገ መግለጫ እሰጣለሁ›› ብለው ነበር፡፡
ዛሬ ቢቢሲ ባወጣው ዘገባ ታዲያ አሜሪካ ‹‹ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢራን ጋር ትክክለኛ ድርድር እፈልጋለሁ›› ማለቷ ተሰምቷል፡፡

በእርግጥ ወደ ድርድር አምርተው ውጥረቱ ይረግብ ይሆን? የቢቢሲ ዘገባ ብዙም ያለው ነገር የለም፡፡ የሁለቱን ሀገራት መካረር ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀቡ ግን እየተገለጸ ነው፡፡ ሀገራቱ በየፊናቸው ወዳጆቻቸውን የማሰባሰብ ሥራ ላይ መጠመዳቸውም እየተነገረ ነው፡፡

ኢራን የአሜሪካ የኢራቅ ቆይታ እንዲጠናቀቅ እንደምትፈልግ እየገለጸች ነው፤ አሜሪካ ደግሞ በዚያ አካባቢ መቆየት እንደምትሻ እየተናገረች ነው፡፡ ድርድሩ እነዚህን ፍላጎቶች ያካተተ ይሁን ወይስ የቆየውን የኑክሊዬር ማብላላት ጉዳይ ብቻ ይሁን የተባለ ነገር የለም፡፡

Iran’s Supreme Leader Ali Khamenei described the missile attacks as a “slap in the face” for the US and called for an end to the American presence in the Middle East.The US strike on Soleimani also killed members of Iran-backed Iraqi militias, who have also vowed revenge. However, US Vice-President Mike Pence told CBS News that “intelligence” indicated that Iran had asked its allied militias not to attack US targets. The US House of Representatives has scheduled a vote for Thursday on limiting President Donald Trump’s ability to wage war against Iran without specific approval from Congress.

https://www.bbc.com/news/world-us-canada-51043559