የኑሮ ውድነቱ የኤክሳይዝ ታክስ ጭማሪው ከፀደቀ በኋላ ይንራል መባሉ ህዝቡን አሳስቦታል።

የኑሮ ውድነቱ የኤክሳይዝ ታክስ ጭማሪው ከፀደቀ በኋላ ይንራል መባሉ ህዝቡን አሳስቦታል።

የተመቻቸው በሕዝብ ገንዘብ ፖለቲካውን እየለጠጡ የህዝብን ሰላም ያናጋሉ። ይህም ያልበቃቸው የመንግስት ፖለቲከኞች በሕዝብ ላይ ተጨማሪ የኑሮ ውድነት አደጋ ደቅነዋል። በጀቶች ሁሉ እየሞተ ያለውን ኢኮኖሚ ከመደጎም ይልቅ ለፖለቲካ ድጎማ መዋሉ ችግሩ እንዲወሳሰብ አድርጎታል። ቅንጦት በሚል የማጭበርበሪያ ቃል የታጀበው አዋጅ የሕዝብን ፍላጎት ያላገናዘበና ያልተጠና ሲሆን በ አበዳሪ አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጫና የሚተገበር አደገኛ አካሔድ ነው።

ስኳርና ዘይት የኤክሳይዝ ታክስ ጭማሪው ከፀደቀ የዋጋ ጭማሪ ይደረግባቸዋል ። መንግስት በሃገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጪ በሚገቡ የተመረጡ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ ጥሏል። ….. በ100 ብር ይሸጥ የነበረ 1 ሊትር ዘይት 140 ብር …. 45 ይሸጥ የነበረው 1 ኪሎ ስኳር 52 ብር ……. 12 ብር የሚሸጥ ለስላሳ 15 ብር ይገባል፤10 ብር የነበረ 1 ሊትር የታሸገ ውሃ 11.50 ብር ……. 15 ብር የነበረው ቢራ 19.50 …. ሸቶዎች፣ የቁንጅና እና መኳኳያ ምርቶች … ዋጋው በእጥፍ ይጨምራል … ሂዩማን ሄር፣ ቅንድብ፣ የእንስሳት ጸጉር እና የመሳሰሉት…. ( https://mereja.com/amharic/v2/184297 ይመልከቱ)

መንግስት የራሱን ገቢ ለማሳደግ በሚሮጥበት ወቅት የሕዝብን ፍላጎት መለካት አልቻለም። ይህ ታክስ የሐገር ውስጥ አምራቾችን ያበረታታል ቢባልም የሃገር ውስጥ ምርቶች የሕዝቡን የፍላጎት ኮታ ምን ያህል ያሟላል የሚለውና የጥሬ እቃ ምንጮችን ታክስ አስመልክቶ የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ አልቻለም። የሐገር ውስጥ አምራቾች ምርቶቻቸውን ለመስራት ከውጪ የሚያስገቡት ጥሬ እቃ ላይ መንግስት የሚያስከፍለው ታክስ ቢሰላ እንዲሁም የምርቶቻቸው ጥራትና አነስተኛነት ቢለካ በሃገሪቱ የኑሮ ውድነትን ማስከተሉ አይቀርም። የምርት እጥረት ሲኖር ፍላጎት ሲጨምር የዋጋ መጨመርና ምርትን የመያዝ ስልቶች በነጋዴዎች ሊደረግ ይችላል ብሎ መገመትም ያስፈልጋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የሐገር ውስጥ አምራቾችም የኤክሳይዝ ቀረጥ እንደማይቀርላቸው መታወቅ አለበት።

መንግስት የሕዝብን ፍላጎትና ወቅታዊ የሕዝብን ኑሮ ያላገናዘቡ አዋጆችን በማፅደቅና በሕዝብ ትከሻ ላይ በማስሀከም ባለፉት አመታቶች ያመጣው ለውጥ የለም። እንደ አለም ባንክና አይ ኤም ኤፍ የመሳሰሉ የፋይናንስ ተቋማትና አማካሪዎቻቸው በሚያቀርቡት ግዴታ ብቻ ብድር ለማግኘት ሲባል የሐገርን ኢኮኖሚና የሕዝብን ኑሮ መግደል ወንጀል ነው። ሊታሰብበት ይገባል። #MinilikSalsawi