የግብፅ፣ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የዩናይትድ ስቴትስና የዓለም ባንክ የጋራ መግለጫ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ የጋራ መግለጫ ወጣ።
የግብፅ፣ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የዩናይትድ ስቴትስና የዓለም ባንክ የጋራ መግለጫ

የግብፅ፣ የኢትዮጵያና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ እንዲሁም ልዑኮቻቸው ከዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትርና ከዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ጥቅምት 26/2012 ዓ.ም. ተገናኝተዋል።

በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ አሞላል እና ማንቀሳቀስ (ኦፕሬሽን) ላይ አጠቃላይ፣ የትብብር፣ የተቀናጀ፣ ዘላቂና ሁሉም ተጠቃሚ ለሚሆኑበት ስምምነት እንዲሁም ይህንን ፅኑ አቋማቸውን በ2008 ዓ.ም. የመርኆች መግለጫ መሠረት ተግባራዊ የሚያደርጉበትን ግልፅ ሂደት ለመፍጠር ቁርጠኛነታቸውን ሚኒስትሮቹ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በውኃ ሚኒስትሮቻቸው ደረጃ የሚካሄዱ አራት መንግሥታዊ የቴክኒክ ስብሰባዎችን ለማድረግ የደረሱበትን ስምምነት አስታውሰዋል።

የዓለም ባንክና ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ እንዲሰጡና በየስብሰባዎቹ ላይም በታዛቢነት እንዲገኙ ሚኒስትሮቹ ተስማምተዋል። ሚኒስትሮቹ በተጨማሪም ስምምነቱን እስከ ጥር 6/2012 ዓ.ም. ለማጠናቀቅ ለመሥራት፣ እንዲሁም ኅዳር 28/2012 ዓ.ም. እና ጥር 4/2012 ዓ.ም. ሂደቱን ለመገምገምና ለመደገፍ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በሚደረጉ ሁለት ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ተስማምተዋል።

እስከ ጥር 6/2012 ዓ.ም. ስምምነት ላይ የማይደረስ ከሆነ የ2008 ዓ.ምቱ የመርኆች መግለጫ አንቀፅ 10 ተግባራዊ እንዲሆን ሚኒስትሮቹ ተስማምተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ስምምነታቸውን ሲያጠናቅቁ ለግብፅ፣ ለኢትዮጵያና ለሱዳን ሕዝቦች የአባይን የጎላ የልማት ትርጉም፣ የወሰን ተሻጋሪ ትብብርን አስፈላጊነት እና ስምምነት ላይ ለመድረስ ያላቸውን የጋራ ፍላጎት በድጋሚ አረጋግጠዋል።