በመንግስት ጥፋት የሕዝብ ገንዘብ የባከነበት የሲዳማው ሪፍረንደም


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በመንግስት ጥፋት የሕዝብ ገንዘብ የባከነበት የሲዳማው ሪፍረንደም

ሲዳማ ጠቅላይ ግዛት ነው፤ ሲዳማ ክፍለ ሃገርም ነው፤ ሲዳማ ትልቅ ሕዝብ ነው፤ ሲዳማ በጠባብነት ብልቃጥ ውስጥ የማትከተው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ ነው፤ እንደዛሬው በገዢዎቹ ሳይቆራረስ ሲዳማ ትልቅ አገር ነበር፤ ስለ ሲዳማ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል።

ካለሪፍረንደም ክልል ማድረግ እየተቻለ ፤ ካለሪፍረንደም ራሱን እንዲያስተዳድር ማድረግ እየተቻለ፤ ብዙ ብዙ ነገር ማድረግ እየተቻለ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ ሪፍረንደም ማካሔድ መንግስት ምን ያህል የፖለቲካ ድድብና እንደተጠናወተው ያሳያል። ባለፈው ጊዜ የተከሰተው ግጭትም የመንግስት ንዝሕላልነት ውጤት ነው።በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ ጉዳዮችን አስፍቶ በማስኬድ ግጭት መፍጠር የመንግስት አካሔድ መሆኑ በየክልሉ እያየን ነው።

ለሪፍረንደም የወጣው ገንዘብ ለሲዳማ ሕዝብ ሆስፒታል፣ ትምሕርት ቤት አሊያም ሌላ ተመራጭ የሆነ የልማት ተቋም ይገነባል። ይህ ለሪፍረንደም የወጣው ገንዘብ ስራ አጥ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ይችላል።

ሕዝቡ በራሱ ክልልነቱን ካረጋገጠ ቆይቷል፤ ይህንን መንግስትም እያወቀ ሪፍረንደም ማድረጉ ከብክነት ውጪ ምንም አይፈይድም። የሕዝብ ገንዘብ የባከነበት የሲዳማው ሪፍረንደም ዞሮ ዞሮ ውጤቱ የሲዳማ ክልልነትን አያስቀረውም። መንግስት ባልተጠና ፖሊሲ ወደ ፖለቲካ ኪሳራ ሲገባ በተደጋጋሚ እየተመለከትን ነው። #MinilikSalsawi