በዋግ ኸምራ የተከሰተው ድርቅ ጊዜ የማይሰጠው ነው ተባለ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በዋግ ኸምራ የተከሰተው ድርቅ ጊዜ የማይሰጠው ነው ሲል የገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴው ገለጸ

(አሥራት) የገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴው አባል አቶ ወንድሙ ካባው በዋግ ኸምራ ስለተከሰተው ድርቅ እንደገለጹት፤ አሁን ላይ በአካባቢው ድርቅ የተከሰተው ከዚህ ቀደም ሲከሰቱ ከነበሩት የተለየ ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም ድርቅ ሲከሰት እርስ በእርሱ እየተረዳዳ የሚያሳልፍ የነበረ ቢሆንም በ2011 ዓመተ ምህረት በወቅቱ ዝናብ ባለመጣሉ ችግሩ አስከፊ መሆኑን ለአሥራት ገልፀዋል።

እስካሁን ድረስ በድርቁ ለተጓዱ ሰዎች በሀገር ውስጥ 220ሺ ብር ከሀገር ውጭ ደግሞ በጎፈንድሚ 3800$ ማሰባሰብ እንደቻሉ አቶ ወንድሙ ገልፀዋል። እርዳታውን በቶሎ ወደ ዞኑ በመላክ እና በጣም የባሰበትን አካባቢ በማገዝ እንደሚጀመሩ እና ሙሉ ለሙሉ መፍትሔ እስከሚያገኝ የሰብዓዊነት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስተባባሪው ተናግረዋል።

መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም በእንዲህ አይነት በጎ ተግባር በመደገፍ እና በማስተባበር የሚታወቁ ዜጎች በድርቅ ለተጓዱ ዜጎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ከ126 ሺ በላይ ዜጎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው መገለፁ ይታወሳል።