ጠ/ሚ አብይ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠ/ሚ አብይ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ውይይት አደረጉ፡፡

በውይይቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 100ኛውን የኖቤል የሰላም ሽልማት በማግኘታቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሜሪካ ታሪካዊውን የለውጥ ሂደት እንደምትደግፍ ጠቅሰው፥ በአሜሪካና ኢትዮጵያ መካከል ስላለው ጠንካራ ወዳጅነት አስፈላጊኒት አንስተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩና ማይክ ፓምፒዮ በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ እንዲሁም ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው መወያየታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል፡፡

በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነትና የጥምር መንግስቱ ተግባራዊ እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማይክ ፖምፒዮ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Source (ኤፍ.ቢ.ሲ)


► መረጃ ፎረም - JOIN US