" /> ሀገራዊ ምርጫ ህዝባዊ ተዓማኒነት እንዲኖረው 250 ሺህ ምርጫ አስፈጻሚዎች ያስፈልጋሉ ተባለ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ሀገራዊ ምርጫ ህዝባዊ ተዓማኒነት እንዲኖረው 250 ሺህ ምርጫ አስፈጻሚዎች ያስፈልጋሉ ተባለ

ለቀጣዩ ምርጫ በ48 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች 250 ሺህ ምርጫ አስፈጻሚዎች ያስፈልጋሉ ተባለ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ አስፈጻሚዎችን የሚመልምል ብሔራዊ ግብረ ሐይል እንደሚያቋቁም አስታውቋል።

ከ48 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ምርጫን የሚያስፈጽሙ አካላትን ለመመልመል ብሔራዊ ግብረ ሐይል ይቋቋማል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት ፣ በ2012 ዓ.ም የሚካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ ህዝባዊ ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ 250 ሺህ ምርጫ አስፈጻሚዎች እንፈልጋለን ብለዋል።

በዘንድሮ ምርጫ ዘመን አዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ከፍተኛ ወጪ እና በርካታ የተማረ የሰው ሐይል ስለሚጠይቅ መጠቀም አልቻንም ፣ ቢሆንም የምርጫ ውጤት አገላለጽን በተመለከተ እንደዚህ ቀደሙ አይዘገይም ብለዋል ሰብሳቢዋ።

ለምርጫ ምዝገባ እና ድምጽ የአሰጣጥ ሂደት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ያልተቻለበት ዋና ምክንይት 80 ሚሊየን ዶላር ወጪ በማስፈለጉ እና ወጪውን ለመሸፈን መንግስት አቅም በማጣቱ እና ከተባባሪ ድርጅቶች ድጋፍ ማግኘት በአለመቻሉ መሆኑን ወይዘሪት ብርቱካን ተናግረዋል ።

በምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፖርቲዎችን የመመዝገቡ ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሆነ እና አንዳንድ ፖርቲዎች አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ አሟልተዉ ሰለማይገኙ የምዝገባ ሥራዉን ወደ ኋላ እያስቀረብን ነው ብለዋል ወይዘሪት ብርቱካን፡፡

ETHIO FM 107.8


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV