ጥቅምት 2 በመስቀል አደባባይ ለሚደረገው ሰልፍ ዝግጅቱ ተጧጡፏል

ለጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ሕዝብ ራሱ ቀስቃሽ ፣ ራሱ አስተባባሪ ፣ ራሱ ሰላም አስጠባቂ ሆኖ ድምጹን የሚያሰማበት ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ትዕይንት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ጥቅምት 2 ለማካሄድ ዝግጅቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

በጋዜጠኛ እና በሰብዓዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ የሚመራው የባላደራው ምክር ቤት ፤ ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሚመለከተው ክፍል ጋር ጉዳዩን አስመልክቶ በደብዳቤ እና በቃል ገለፃ መደርጉ ለማወቅ ተችሏል ።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፤በአዲስ አበባ በተላለያዩ አካባቢዎች ለጥቅምት 2 ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ ወጣቶች በስፊው እየተዘጋጁ ነው።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV ON YOUTUBE