" /> ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጋራ ምክር ቤቶች ባደረጉት ንግግር ትኩረት ካደረጉባቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጋራ ምክር ቤቶች ባደረጉት ንግግር ትኩረት ካደረጉባቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጋራ ምክር ቤቶች የዓመቱ የሥራ መጀመሪያ ስብሰባ ላይ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ባደረጉት ንግግር ትኩረት ካደረጉባቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

•በዓመቱ ለመሥኖ ሥራዎች ትኩረት በመስጠት ለሥራ ዕድል ፈጠራም ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይደረጋል፤ በዚህም 12 ሺህ የተማሩ ወጣቶችን ሊያስተናግድ የሚችል የመሥኖ ልማት ሥራ ይከናወናል፡፡

•የሀይል መቆራረጥን ለመቀነስ የተሻሉ ቴክኖሎጂዎችን ከመተግበር ባሻገር የመስመር፣ የትራንስፎርመር እና የቆጣሪዎች ምርመራ እና ማሻሻያ ይደረጋል፡፡

•የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን በተመለከተ በገጠር 50 ሺህ የሚጠጉ አዳዲስ የመጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ፣ ከ13 ሺህ በላይ የማይሰሩ ተቋማት መልሶ የማቋቋም፣ በከተማ ደግሞ 60 አዳዲስ የመጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ እና 30 ደግሞ መልሶ የማቋቋም ሥራ ይከናወናል፡፡

•በድርቅ በሚጠቁ አካባቢዎችም የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን ለማሳካት ይሰራል፡፡

•ቁልፍ የመንግስት አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ዘርፎች በተሻለ ቴክኖሎጂ ለማደራጀት ይሰራል፤ ይህም የጊዜ፣ የሀብትና የሰው ሃይል ብክነትን ይቀንሳል፡፡

•የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሳተላይት በያዝነው ዓመት በታህሳስ ወር በቻይና ከሚገኝ የጠፈር ማዕከል ወደ ጠፈር የሚላክ ይሆናል፡፡ ይህም ለግብርና፣ ለደን ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ የሚስፈልጉትን የሳተላይት መረጃዎች ለመቀበል ይውላል፡፡ ሳተላይቱን በራሳችን ባለሙያዎች የምንቆጣጠርበት ጣቢያም እንጦጦ ላይ ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

•የኢንፎርሜሽንና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፉን ለማሳደግ በያዝነው በጀት ዓመት ሁለት ተጨማሪ የቴሌኮም ኦፕሬተሮችን አወዳድሮ ፈቃድ በመስጠት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ሦስት ኦፕሬተሮች እንዲኖሩ ይደረጋል፡፡ በዚህም የግሉ ዘርፍ በኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂው ዘርፍ እንዲሳተፍ ይደረጋል፡፡

EBC


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV