እስቲ ላቲንን ከኢትዮጵያ ፊደል እናወዳድር – በመረጃና ሳይንስ እንነጋገር #ግርማካሳ

“አመሰግናለሁ” በላቲን “galatoomaa” ነው። በ ኢትዮጵያ ፊደል ደግሞ “ገለቶማ” ነው። በላቲን 10 ፊደላት ሲፈጅ በግ እዝ 4 ብቻ ነው የሚፈጀው። ከእጥፍ በላይ።

“galatoma” , “galatooma”, “galatomaa” አይደለም። “galatoomaa” ነው። ስፔሊንግ ላይ ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ የግድ ነው። እንደ ኢትዮጵያ ፊደል እንደ ሰማነው ልንጽፍ አንችልም።

“በጣም አመሰግንዎታለሁ” ወይም “በጣም አመሰግናቹሃለሁ” ማለት ደግሞ በኢትዮጵያ ፊደል ፣ “ባይ ኤን እስን ገለቴፈደ” ነው። 13 ፊደላት ያስፈልጋሉ። በላቲን “Baay’een sigalateeffadha” ነው። 23 ፊደላት ያስፈልጋለኡ። በግእዝ ለመጻፍ ከሚያስፈልገው ሁለት እጠፍ ማለት ነው።

አሁን አንድ የላቲን ተማሪ፣ “Baay’een sigalateeffadha” እጽፋለሁ ብሎ፣ “Bay’een sigalateeffadha”፣ “Baay’en sigalateeffadha” ፣ ” Baay’een sigalateffadha”፣ “Baay’een sigalateefadha” ወይም “Baay’een sigalateeffadha” ሊጽፍ ይችላል። ኮንሶነቶች ከቫወሎች እንዴት እንደሚጻፉ ስፔሊንጉን በሚገባ ጠንቅቆ ካላወቀ።

እንግዲህ ፍረዱ። ለሌላው ፊደልን ለሚያውቅ ፣ አማርኛ፣ ትግሬኛ፣ ጉራጌኛ በኢትዮጵያ ፊደል ማንበብና መጻፍ ለሚችል፣ ኦሮምኛ መማር ካስፈለገው፣ ኦሮሞኛ እንዲማር የቱ ነው የሚቀለው ??????

ሌላ ልጨምርላችሁ። “አዎ” በኦሮምኛ በኢትዮጵያ ፊደል ” ኤዬ” ነው። በላቲን ደግሞ ሶስት እጥፍ ፊደል እንጠቀማለን። ” Eeyyee” ነው።

ኦሮምኛ በኢትዮጵያ ፊደል መጻፍ አይቻልም የሚሉ፣ እንዳንድ ለአማርኛ፣ ለግእዝ ፣ ኢትዮጵያዊ ለሆነ ነገር አለርጂክ የሆኑ ዘረኞች ሲያጭበረበሩና ሲዋሹ ብዙ ጊዜ ይሰማሉ። ያንን ማድረጋቸው አያስደንቅም። ለምን በሐሳብ መሞገት የማችል፣ መረጃና ሳይንስ ይዞ መከራከር የተሳነው ሰው፣ የሚኖረው ምርጫ ነገሮችን መሸፋፋእን፣ መዋሸትና ማምታት ነው።

ከዚህ በታች ያለው ዝግጅት አቶ በቀለ ገርባ በመቀሌ በተናጋሩት አንድ ዝግጅት ላይ፣ የኢትዮጵያ ፊደል ለኦሮምኛ ብቃት የለውም ብለው በሰጡት አስተያየት ዙሪያ የተዘጋጀ ቅንብር ነው። በዚህ ቅንብር ሳይሳንሳዊ በሆነ መልኩ ከላቲን ፊደል ይልቅ የኢትዮጵያ ፊደል በ እጅጉ ለመማርና ለማስተማር የተሻለ እንደሆነ ምሁራን ያስረዳሉ።