ፀረ-ሽብር ሕግን ጠቅሶ መክሰስ ተስፋ የተጣለበትን ለዉጥም ሊያደናቅፈዉ ይችላል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


DW : «አፋኝ» ተብሎ የሚወቀሰዉን የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብር ሕግን ጠቅሶ ተጠርጣሪዎችን ማሰርና መክሰስ የፍትሕ ስርዓቱን ለማሻሻል የሚደረገዉን ጥረት የሕዝብ አመኔታ ሊያሳጣዉ እንደሚችል አንዲት የሕግ ባለሙያና ሌላ ጋዘጠኛ መከሩ።የሕግ ባለሙያና ጠበቃ አዲስ መሐመድ እንደሚሉት ተጠርጣሪዎችን «ይሻሻላል» የተባለዉን ፀረ-ሽብር ሕግን ጠቅሶ መክሰስ ተስፋ የተጣለበትን ለዉጥም ሊያደናቅፈዉ ይችላል።ግዮን የተባለዉ መፅሔት ዋና አዘጋጅ ሮቤል ምትኩ በበኩሉ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን በፀረ-ሽብር ሕጉ መክሰስ «ስሕተት ነዉ» ይላል።