በክልል ለመደራጀት ያቀረብነው ጥያቄ በጥናት ለመመለስ የሚደረገውን አካሄድ እንቃወማለን


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በክልል ለመደራጀት ያቀረብነው ጥያቄ ከሕገ መንግሥታዊ ስርዓት ውጭ በጥናት ለመመለስ የሚደረገውን አካሄድ እንቃወማለን

DW : የዎላይታ ሕዝብ በክልል ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ ከሕገ መንግሥታዊ ስርዓት ውጭ በጥናት ለመመለስ የሚደረገውን አካሄድ እንደማይቀበለው የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) አስታወቀ። የንቅናቄው ይህን ያስታወቀው የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወቅታዊ ጉዳይ በሚል ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ የዎላይታ ህዝብ የራሱን ክልል ለመመሥረት ያቀረበው ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ ተግባራዊ እንዲሆን ጠይቋል።

በአሁኑ ወቅት ክልሉን በገዢ ፓርቲነት በሚያስተዳድረው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( በደኢህዴን ) እየተደረገ ለሚገኘው የክልል መዋቅር ጥናትም ሆነ ውጤት እውቅና እንደማይሰጥ ንቅናቄው አስታውቋል። ይሁን እንጂ ጥያቄው ህጉ በሚፈቅደው መሰረት በአካባቢ ምክር ቤቶች ጸድቆ ባለፈው ታህሳስ ወር ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ቢላክም አስከአሁን ምላሽ አለተገኘም ሲሉ የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶከተር አበባየሁ ቶራ ለዶቼ ቨለ ( DW ) ገልጸዋል። ንቅናቄው በዚሁ መግለጫው በአሁኑወቅት ክልሉን በገዢ ፓርቲነት በሚያስተዳድረው የደቡብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( DW ) እየተደረገ ለሚገኘው የክልል መዋቅር ጥናትም ሆነ ውጤት የንቅናቄው እውቅና አይሰጥም ሲል አመልክቷል ።

Äthiopien, Sidama und Wolaita Versöhnung (DW/S. Wegayehu) ይህ ማለት ምን ማለት ነው? በሚል ከዶቼ ቨለ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሊቀመንበሩ ሲመለሱ በአጭሩ በክልል የመደራጀት ጥያቄያችን ጥናት አያሰፈልገውም ማለት ነው ብለዋል።

የፌደራሉ መንግስት በክልል ለመደራጀት ጥያቄ ያቀረቡ ዞኖች በትዕግስት ጠብቁ በሚል ባቀረበው ጥሪ ዙሪያ የንቅናቄያችሁ አቋም ምንድነው በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶከተር አበባየሁ የፌደራሉ መንግስቱ ዋና ስራ ህገ መንግስቱን ማክበርና ማስከበር ብቻ ነው ሲሉ መልሰዋል። ዶቼ ቨለ ( DW) በንቅናቄው መግለጫ ዙሪያ ክልሉን በገዢ ፓርቲነት እያስተዳደረ የሚገኘውን የደቡብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ደኢህዴን ) አመራሮችን አስተያየት ለማካተት ያደረገው ሙከራ የእጅ ስልካቸው ጥሪ ባለመመለሱ ምክንያት ሊሳካ አልቻለም ።
በደቡብ ክልል አስር የዞን መስተዳድሮች እራሳቸውን በከፊል ራስ ገዝ ወይም ክልል ለማደራጀት ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየጠበቁ እንደሚገኙ ይታወቃል። በተለይም ከዞኖቹ የቀረበው ጥያቄ ከሳምንት በአገሪቱ የመወሰኛ ምክር ቤት ቀርቦ ጠቅላይ ሚንስተሩ ምላሽ ከሰጡበት ወዲህ ጉዳዩ ዳግም አነጋጋሪ እየሆነ ይገኛል። ከወላይታ በተጨማሪ በሲዳማ ዞን የሚንቀሳቀሱ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲዳማ ህዝብ በክልል ለመደራጀት የቀረበውን የህዝበ ውሳኔ ቀን በአስቸኳይ ይፋ እንዲደረግ ሲሉ ባለፈው ማከሰኞ ተመሳሳይ ጥያቄ ማቅረባቸው ማቀረባቸው ይታወቃል። ክልሉን ገዢ ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ደኢህዴን ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ካለፈው ዓርብ ጀምሮ በስብሰባ ላይ መሆናቸው ቢነገርም አስከአሁን ግን በስብሰባው ውጤት ዙሪያ የተሰጠ ኦፊሴላዊ መግለጫ የለም።