የአዴፓ/አማራ ክልል ሃላፊዎች ሰልፈኞችን ወጥተው ለማናገር ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

በአማራ ክልል በበርካታ ከተሞች ደማቅ ሰላማዊ ሰልፎች ተደርገዋል። ሰልፎቹ የተደረጉት በቤኒሻንጉል ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ ቀድሞ ብአዴን ተብሎ የሚታወቀውና አሁን አዴፓ ብሎ ራሱን የሰየመው ክልሉን የሚያስተዳድረ ድርጅትን አካሄድ በመቃወም ነው። ሰልፈኞቹ በቅርቡ በአጣዬና አካባቢዎች በኦነግ ታጣቂዎች በደረሰው ግፍና ሰቆቃ የክልል መንግስቱ  ከንፈር ከመምጠትና ላይ ላዩን ሃዘኔታ ከመግለጽ ባለፈ ምንም ማድረግ እንዳልቻለ የገለጹ ሲሆን፣  አሁንም በቤኒንሻጉል በአማራ ተወላጆች ላይ ለደረሰው ጥቃት አዲስ ሳይሆን የተለመደ እንደሆነ እንደሆነ ይናገራሉ።

ሰለፈኞቹ በባህር ዳር የአማራ ክልል ርእስ መስተዳደር  ጽ/ቤት ሲደርሱ ወጥቶ ጥያቄዎቻቸው ለማዳመጥ የወጣ ባለስልጣን  ስለመኖሩ  መረጃ ለሰልፈኞች ባቀረበው ጥያቄ ፣  “ቁጥሩ ቀላል የማይባል ህዝብ ድምጹን ለማሰማት በሚመጠበት ጊዜ፣ የሕዝብ ተወካይ ነን እያሉ፣ እንኳን ሊያናግሩን እዚህ ግንቡ ውስጥ ተደበቀው ነው  እያዩን ያሉት”  ሲሉ በሰለፉ የተገኙ አንድ እናት ሲናገሩ፣ ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል ያለ አንድ ወጣት ” እነርሱማ ጭራሽ ሕዝቡ ሕገ መንግስታዊ መብቱን እንዳይጠቀም ሰው ሰልፍ እንዳይወጣ ሲያከላክሉ ነበር” የሚል ምላሽ ነው የሰጠው።

እንዳጋጣሚ ባህር ዳርን ለመጎብኘት ከአሜሪካ የመጡ  በሰልፉ አካባቢ የነበሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ፣ በዋሺንግንት ዲሲ ኢትዮጵያዉያን የተቃወሞ ሰላማዊ ሰልፍ በዉጭ ጉዳይ መስሪያ ሲያደርጉ ሁልጊዜ የስቴት ዲፓርትምነት ሃላፊዎች ወጥተው ደብዳቤዎችን እንደሚቀበሉና ሰልፈኞችን ለማነጋገር እንደሚሞክሩ አስረድተው፣ “ይሄ ሁሉ ሕዝቡ መጥቶ ከክልሉ ርእስ መስተዳደር ጽ/ቤት ዋና ሃላፊዎችም ባይሆንም፣  ታች ያሉ ተራ አመራሮች ወጥተው የህዝቡን ጥያቄ እንደሰሙ መናገር አለመቻላቸው ለሕዝብ ያላቸውን ትልቅ ንቀት የሚያሳይ ነው” ሲሉ ለመረጃ ገልጸዋል።

በሰልፉ አንዲት ጠጠር እንዳልተወረወር፣ ምንም አይነት በሰው ሕይወት ላት ጥፋት እንዳልደረሰ፣ ምን አይነት ንብረት እንዳልወደመ የገለጹት ሰልፈኞች ሰልፉ በሰላም ተጀምሮ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

የከተማዋ ፖሊስና የክልሉ የሕግ አስከባሪ ሃይላት በሰልፈኞች ላይ ምንም አይነት ትንኩሳም ሆነ ችግር እንዳልፈጠሩ መረጃ ያረጋገጠ ሲሆን፣ ሰልፈኞችን ለሕግ ስከባሪ አባላት ያላቸውን ክብርና አድናቆትም እንዳላቸው ለመረጃ ገልጸዋል።

በሁለት ወራት በፊት ከአቶ ገዱ የተሻሉ ይሆናሉ ተብለው በተጠበቁትና የክልሉ ርእስ መስተዳደር   በሆኑት በዶ/ር አምባቸው መኮንን ሰልፈኞች ከማዘን አልፎ ውስጣቸው በጣም እንደተሰበረ ነው ለመረጃ የገለጹት። አንድ የከተማዋ ነዋሪ እንደሆኑ የገለጹት አባት፣  “ዶ/ር አምባቸው  በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሄን ያህል ተቃወሞ ማስተናገዱ በግሌ አሳዝኖኛል። በአካሄዱ ደስተኛ አይደለሁም” ሲሉ ዶ/ር አምባቸው የማስተዳድረ ሕዝብ ምን ይላል የሚል ሳይሆን የኢሕአዴግ ድርጅቴ ምን ይላል ለሚለው ቅድሚያ እንደሚሰጡ ነው ለመረጃ የገለጹት።