ሶስት አራተኛ የከሚሴ/ባቲ ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ፣ ግን የስራ ቋንቋው ላቲን#ግርማካሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በአማራ ክልል “በርከት ያሉ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ያሉበት ነው” በሚል ሶስት ወረዳዎች የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን በሚል ልዩ መስተዳደር ውስጥ ተካተዋል። እነዚህ ወረዳዎች የአርጡማ ፉርሲ፣ የባቲና የጨፌ ጎላና ወረዳዎች ናቸው። የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ተብሎ ዞኑ ለኦሮሞዎች በሚል ቢሸነሸንም ፣ አንደኛ ዞኑ በአማራ ክልል መስተዳደር ስር ያለ ዞን ነው። ሁለተኛ በዞኑ ኦሮምኛ ተናጋሪ ያልሆኑ ማህበረሰብት በብዛት አሉበት።

በኢሕአዴግ ዘመን ሁለት የሕዝብ ቆጠራዎች ተደርገዋል። አንደኛው እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ1994 ዓ.ም የተደረገ ሲሆን ሁለተኛው በ2007 ዓ.ም የተደረገ ነው። የ2007 የሕዝብ ቆጠራ ውጤት በወረዳና በከተማ ደረጃ የዜጎች የአፍ መፍቻ ቋንቋ ምን እንደሆነ በሪፖርቱ ይፋ አላደረገም። ይሄን የሆነበት ምን አልባት ከፖለቲካ ዉሳኔ የተነሳ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ። ከዚህም የተነሳ በ1994ቱ የሕዝ ቆጠራ ውጤት የተቀመጡ ቀመሮችን እንደ ግባት በመውሰድ አንዳንድ ሐሳቦችን ለማስቀመጥ እሞክራልሁ።

በባቲ ወረዳ፣ በ1994 የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሰረት ወደ 144904 ሺህ ነዋሪዎች ነበሩ። ከነዚህ ነዋሪዎች 51.1% የሚሆኑት የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አማርኛ ነው። 48.3% ደግሞ ኦሮምኛ። ስለዚህ ወረዳው ሕብረ ብሄራዊ ወረዳ ነው ማለት ነው። በወረዳው ያሉ ሶስት ከተሞችን ብንወስድ ኦሮምኛ ተናጋሪው እጅግ በጣም ጥቂት ነው። በባቲ ከተማ 17.7%፣ በገብራ ከተማ 2.4%፣ በደገን ከተማ ደግሞ 0.2%። ያ ማለት በባቲ ከተማ ከ75% በላይ፣ በገብራና በደገን ደግሞ ከ96% በላይ ነዋሪዎች አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው ማለት ነው።

የአርጡማ ፋርሲን ወረዳ ብንወስድ 80% ነዋሪው፣ አብዛኛው በገጠር የሚኖር፣ ኦሮምኛ ተናጋሪ ነው። ወደ 20.3% አማርኛ ይናገራል። በወረዳዉ ሁለት ትላልቅ ከተሞች፣ ጨፋ ሮቢትና ሰንበቴ ከ70% በላይ ነዋሪው አማርኛ ተናጋሪ ነው።
ጨፌ ገለና ወረዳ ስንሄድ፣ ከ34% በላይ ነዋሪው ኦሮምኛ ተናጋሪ አይደለም። ከሜሴ ከተማ የወረዳው ብቻ ሳይሆን የዞኑን ዋና ከተማ ናት። በከሚሴ ኦሮምኛ ተናጋሪው አንድ አራተኛ ብቻ ነው። ከ73% በላይ ነዋሪው የአፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛ ነው።

እንግዲህ እዉነታው ይሄ ሆኖ እያለ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ተብሎ በተሸነሸነው ዞን፣ ፍጹም ዘረኛና አፓርታይዳዊ የሆነ አሰራር መስፈኑ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም። ዞኑ ምንም እንኳን በአማራ ክልል ስር ተካቶ፣ ባጀት የሚያገኘው ከአማራ ክልል መንግስት ቢሆንም፣ የሚተዳደረውና መመሪያ የሚቀበለው ግን ከኦሮሞ ክልል መንግስት እንደሆነ ነው ብዙዎች የሚናገሩት። በዞኑ ልክ እንደ ኦሮሞ ክልል መንግስት፣ የፌዴራልና የክልል የስራ ቋንቋ በሆነው በአማርኛ ምን አይነት የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ መንግስታዊ አገልግሎት አይሰጥም። በዞኑ በሃላፊነት ላይ የተቀመጡትም የዞኑ ነዋሪዎች ሳይሆን በኦህዴድ/ኦዴፓ የተላኩ ከአርሲና የወለጋ የመጡ ባለስልጣናት እንደሆኑ ነው የሚነገረው። የዞኑ የትምህርት ካሪኩለምም ተዘግጅቶ የሚመጣው ከኦሮሞ ክልል ነው።

ዞኑ ሕብረ ብሄራዊ እንደመሆኑ፣ በዞኑ የሚኖሩ አብዝኛው የባቲ ወረዳ፣ ከሃያን ከሰላሳ በመቶ በላይ የሚሆኑት የአርጡማ ፋርሲና ጨፌ ጉለና ነዋሪዎች አማርኛ እየተናገሩ፣ ወደ ሰባት የሚጠጉ የዞኑ ከተሞች፣ ከቦራ ከተማ በቀር በሁሉም፣ ከሶስት አራተኛ በላይ ነዋሪው አማርኛ ተናጋሪ ሆኖ፣ በአማርኛ አገልግሎት እንዳያገኙ መደረጉ፣ በዞኑና በዞኑ ባሉ ወረዳዎች እንዳይቀጠሩ ማገዱ ስህተት ብቻ ሳይሆን ኦሮምኛ ተናጋሪ ባልሆኑ ወገኖች ላይ የሚፈጸም ግፍ ነው።

የአማራ ክልል መንግስትና አዴፓ ፣. እንደ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ዝዋይ፣ አሰላ፣ ፈንታሌ ወረዳ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ… ባሉ፣ ሕብረብሄራዊ በሆኑ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች፣ ኦሮምኛ የማይናገሩ ማህበረሰባትን መብት ለማስከበር እንሰራለን ሲሉን ነበር። በትንሹ ያልታመነ በትልቁ አይሾምም እንደሚል መጽሐፉ፣ አዴፓ በሚያስተዳድረው ክልል ውስጥ ፍትሃዊነትና እኩልነትን ማስፈን ካልቻለ፣ እንዴት አድርጎ ነው በኦሮሞ ክልል ኦሮሞ ያልሆኑ ሌሎች ማህበረሰባት መብት ማስጠበቅ የሚችለው ?

በኔ እይታ፣ ይሄ በአማራ ክልል ከህዝቡ ፍላጊት ውጭ የኦሮሞ ብሄረተኞች ወሎ የኦሮሞ ነው በማለታቸው ብቻ የተሸነሸነው የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የሚባለው መፍረስ ያለበት ዞን ነው። የባቲ ወረዳ ከደቡብ ወሎ፣ የአርጡማ ፋርሲና ጨፌ ጎለና ወረዳዎችን ከሰሜን ሸዋ ዞን ጋር መቀላቀሉ ጠቃሚ ነው ባይ ነኝ።

ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ብቻ ሳይሆን ኦሮምኛ የማይናገሩ የደቡብ ወሎና የሰሜን ሸዋ ነዋሪዎችም ከአማርኛና ከእንግሊዘኛ በተጨማሪ ኦሮምኛ ወይንም አፋርኛ እንዲማሩ ማድረግ ይቻላል። አማርኛንና ኦሮምኛን ደርቦ ለመማር የሚቀለው ደግሞ እርሱ ስለሆነ፣ በግእዝ ጠል ወገኖች የተጫነውን ላቲንን በመተው፣ ኦሮምኛን ብቃት ባለው በግእዝ ፊደል እንዲሰጥ ማድረጉ እጅግ በጣም አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ቁልፍ ጉዳይ ነው የሚሆነው። ኦሮምኛ ተናጋሪ ያልሆነው ማህበረሰብ፣ የኔም ቋንቋ ነው ብሎ እንዲቀበለውና ፈቅዶና ወዶ እንዲማረው።

አዴፓም ሆነ የአማራ ክልል መንግስት ይሄንን ለማድረግ የሚያግደውም ሆነ የሚከለክለው ምንም ነገር ሊኖር አይገባም። ከዚህ በፊት ብአዴን በራሱ ፍቃድ የሚሰራ ስላልነበረ፣ ለሕዝብ ፍላጎትና ጥቅም የቆመ ሳይሆን ለሕወሃት ታዛኝ ስለነበረ ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ይህን አይነት አፓርታይዳዊና ዘረኛ አሰራር አሜን ብሎ ተቀብሎ ኖሯል።

አሁን ግን በአመራር አላይ ያሉት የአዴፓ ሰዎች የሕዝቡን ጥቅም ለማስጠበቅ የተዘጋጁ እንደመሆኑ ወይም ተዘጋጅተናል እንደማለታቸው፣ ምን አልባት ከኦዴፓ/ኦህዴድ አካባቢ ካሉ ጽንፈኞች የሚመጣውን መሰረት አልባ ቅሬታ በመናቅ ለሁሉም የሚበጀውን፣ የሚጠቅመውን ያደራግሉ ብዬ አስባለሁ።