ለሸዋ የብሄር/ዘር አወቃቀር አይሰራም #ግርማካሳ

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

የሚከተለው ሰነድ የተዘጋጀው እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ 1994 ነው። ይሄን የሕዝብ ቆጠራ ውጤት ዋቢ በማድረግ አንዳንድ ሐሳቦች ለማመላከት እሞክራልሁ።

ከ 1994 ቀጥሎ በ 2007 የተደረገ የሕዝብ ቆጠራ አለ። ሆኖ የቆጠራው ሪፖርት የተሟላ አይደለም። በወረዳ ደረጃ ነዋሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ምን እንደሆነ የ2007 ሪፖርት አላስቀመጠም።

በዚህ ጽሁፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋን እንጂ ማንነት/ብሄር ወይም ethnicity የሚባለው ከግምት አላስገባሁም። አሻሚ ስለሚሆን። ሸዋ ውስጥ ደግሞ የሚኖረው አብዛኛው ቅይጥ ነው። እናቱ አማራ፣ አባቱ ኦሮሞ የሆነ በወቅቱ ኦሮሞም አማራም ብሎ መጻፍ አይቻልም ነበር። ሌላው በኦሮሞ ክልል ስራ ለማግኝት ለመቀጠር ኦሮሞ መሆን ግዴታ ስለነበረ9አሁንም ስለሆነ) አማራ ሆነው ኦሮሞ ነን ያሉም ብዙ ናቸው። ስለዚህ ሳይንሳዊ ያለሆነን ቀመር ላይ ተመርኩዤ አስተያየት መስጠት አልፈለኩም። የአፍ መፋች ቋንቋ ግን አሻሚ ሆኖ አላገኘሁትም።

እንግዲህ በቀዳሚነት ከዚህ የምንማረው የኦሮሞ ማህበረሰብ ምን ያህል ከሌላው ማህበረሰብ ጋር ተደበላልቆ እንደኖረ ነው። ከሌላው ጋር የተሳሰረ ነው።

አሁን በአገራች ችግር እየተፈጠረ ያለው ይሄን የተሳሰረ ማህበረሰብ ለማለያየት እየተሞከረ መሆኑ ነው። በሸዋ ከአማራው፣ ከጉራጌ..የተለየ የኦሮሞ ማህበረሰብ ለመፍጠር የኦሮሞ ብሄረተኞች ደፍ ቀና ይላሉ። መጋብባት እንኳን እንዳይችል ኦሮምኛን የሚያስተምሩት ብቃት ያለው የግእዝ ፊደል እያለ በላቲን ነው።

በሶስት ወረዳዎች፣ ደራ፣ ፈንታሌና የአዳማ ወረዳ ኦሮምኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ያልሆኑ ዜጎች ማጆሪቲ ናቸው። በገራር ጃርሶ ከኦሮምኛ ተናጋሪው እኩል ሲሆኑ፣ በቆቂርና በሎሜ ወረዳዎች ከ40% በላይ ናቸው።

በአዲስ አበባ ዙሪያ በ 1994 የነበረው አብዛኛው የአቃቂ ወረዳ ወደ አ.አ ተቀላቅሏል። ያልተቀላቀለውም ከአዲስ አበባ መስፋፋት ጋር የበለጠ ሕብረ ብሄራዊ እየሆኑ ነው የመጣው። ሙሉ ሱሉልታ ፣ በራና አለልቱ ፣ ጊምቢቹ ፣ ዋልማራ፣ አለም ገና፣ አድአ ፣ ሎሜና ቅምብቢት ወረዳዎች፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ እንደመሆናቸው ፣ አዲስ አበባም ደግሞ ከመጠን በላይ የሰፋች ከተማ እየሆነች በመምጣቷ፣ ኦሮምኛ የአፍ መፍቻ ቋንቃቸው የሆኑ ዙጎች ቁጥራቸው ከሌሎች ጋር ሲነጻጸር በጣም እየቀነሰ ነው የመጣው። ( ከሃረርጌ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች በዚህ አካባቢ ለማስፈር ቢሞከርም፣ ቀመሩን ያን ያህል አይቀይረዉም) ። በአጭር ይህ አካባቢ የተደባለቀ፣ ህብረ ብሄራዊ የሆነ አካባቢ መሆኑ አማርኛ በስፋት የሚነገርበት አካባቢ ነው።

እርግጥ ነው አዲስ አበባ መስፋቷን አንዳንድ የኦሮሞ ብሄረተኞች አይመቻቸውም።ለገበሬው ከማሰብ ሳይሆን የኦሮሚን መልክ እየቀየረ ነው ከሚል ነው ተቃዉሞ የሚያሰሙት። ሆኖም፣ አዲስ አበባም በጣም ሳትሰፋም፣ ከሃያ ሶስት አመታት በፊት፣ እንደ አዳማ ፣ ፈንታሌ. ሎሜ. ቆቂር፣ አለም ገና …ባሉ ወረዳዎችም ኦሮምኛ የማይናገው ማህበረሰብ ቁጥር ቀላል አልነበረም።

ታዲያ ይሄን አካባቢ ኦሮምኛ ብቻ የስራ ቋንቋ በሆነበት፣ መንግስታዊ የክልል፣ ዞን፣ ከተማና ወረዳ መንግስታት በኦሮምኛ ብቻ አገልግሎት በሚሰጡበት፣ ኦሮምኛ የሚናገር ብቻ የመንግስት ሰራተኛም፣ ሆን ባለስልጣን እንዲሆን በሚደረግበት፣ ለኦሮሞ ብቻ ተብሎ በተሸነሸነ ክልል ውስጥ መሆን ነበረበት ???????

የኦሮሞ ማህበረሰብ እንደ ቆቂርና ሶዶ ዳጬ ወረዳዎች ከጉራጌው ጋር ተደባልቋል፤ በፈንታሌ ከአማራውን ከአርጎባው ጋር ተደባልቋል፣ በገራር ጃርሶ፣ በደራ፣ በአቢቹ.…ከአማራው ጋር ተደበላልቋል። ታዲያ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ እያሉ ልዩነት ማድረግ ለኦሮሞዎስ ይበጃል ???????

ይልቅ ኦሮምኛ (በግእዝ ፊደል ተጽፎ) እና አማርኛም የስራ ቋንቋዎች ሆነው፣ ሁሉም እኩል የሚታዩበት፣ ሸዋ በሚል ፌዴራል መስተዳደር ስር መቀጠሉ አይሻልምን ???

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ “የአስተዳደር ወሰን እንጂ ክልል” የለም ነበር ያሉት። እንግዲህ ይሄንን ለርሳቸውም ሆነ የማንነትና ወሰን ጉዳዮች ለሚመለከተው ኮሚሽን ግባት ይሆን ዘንድ ጽፊያለሁ።