የኤርትራው አምባሳደር ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መቀዛቀዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ወቀሱ

በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት እንደ ቀድሞው አለመሆኑን በደቡብ ሱዳን የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት ዮሃንስ ተክለሚካኤል ተናገሩ።
አምባሳደሩ ይህንን የተናገሩት ባልተለመደ ሁኔታ በብሪታኒያ የኤርትራ ኤምባሲ የዩቲዩብ ቻናል ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሲሆን፣ ቪዲዮው ይፋ ከተደረገ ከሰዓታት በኋላ እንዲነሳ መደረጉን ቢቢሲ ትግርኛ አረጋግጧል።